በአካቶ ትግበራ (Gender Mainstreaming) እና የፆታዊ ጥቃት ምንነትና ጉዳቶቹ በሚል ርዕሰ ጉዳይ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ፡፡
ነሐሴ 15/2018 ዓ.ም
በገቢዎች ሚኒስቴር የመካከለኛ ቁ.1 ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት ከየስራ ሂደቱ ለተውጣጡ የሥርዓተ-ጾታ ተወካዮች፣ የሴቶችና ወጣቶች ህብረት ኮሚቴ አባላት እንዲሁም የሶሻል ኮሚቴ አስተባባሪዎች በአካቶ ትግበራ (Gender Mainstreaming) የፆታዊ ጥቃት ምንነት፣ ጉዳቶቹና መፍትሄው በሚል ርዕሰ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡
የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቡድን አስተባባሪ የሆኑት ወ/ሮ አለምጸሀይ ረዳ ስልጠናውን በይፋ ባስጀመሩበት ወቅት የስርዓተ-ጾታ ጉዳይ የአንድ ክፍል ስራ ብቻ እንዳልሆነ ገልጸው ስልጠናውን መስጠት ያስፈለገበት ዋነኛ ዓላማ የስርዓተ-ጾታን ጉዳይ በሁሉም የቅ/ጽ/ቤቱ የስራ እንቅስቃሴ ውስጥ የበለጠ አካቶ ለመተግበር የስርዓተ-ጾታ ተወካዮች፣ የህብረቱና የሶሻል ኮሚቴዎች ከሁሉም የስራ ሂደቶችና ቡድኖች ተወክለው የመጡ በመሆኑ በቀጣይ የሴቶች፣ ወጣቶችና አካል ጉዳተኞችን ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በሚደረግ ጥረት ውስጥ ስለ አካቶ ትግበራ ግንዛቤ አግኝተው እገዛ እንደሚያደርጉ በማሰብ እንደሆነ ገልፀዋል።
ወ/ሮ አለምፀሃይ አክለውም በቅ/ጽ/ቤቱ ካለው አጠቃላይ የሰው ኃይል የሴቶች ድርሻ 55% እንዲሁም የወጣቶች ድርሻ ከ50% በላይ ቢሆንም ከፍ ያሉ የስራ ደረጃዎች ላይ እና ወደ አመራርነት ቦታ ላይ ስንመለከት ቁጥሩ ዝቅተኛ ስለሆነ ሴቶችና ወጣቶችን ወደ አመራር እንዲመጡ ማብቃትና መደገፍ እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።
ስልጠናው በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የሴቶች ህጻናትና ወጣቶች ድጋፍና ክትትል ባለሙያ በሆኑት በአቶ ተሜ አምበሉ አማካኝነት ተሰጥቷል።
August 21, 2026 17.1K 6



