በተሻሻለው የገቢ ግብር አዋጅ 1395/2017 ንዑስ አንቀጽ 29 መሠረት ከዲጅታል ይዘት ፈጠራ ከሚገኝ ገቢ… — M.O.R. Medium Tax Payers No 1 Branch Office — TG.ME

በተሻሻለው የገቢ ግብር አዋጅ 1395/2017 ንዑስ አንቀጽ 29 መሠረት ከዲጅታል ይዘት ፈጠራ ከሚገኝ ገቢ ግብር እንዲከፈልበት ተደርጓል ነሐሴ 26/2018 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር) በዚሁም መሠረት ከዲጂታል ይዘት ፈጠራ የሚገኝ ገቢ ማለት አንድ ግለሰብ፣ ድርጅት የቪዲዮ ማጋሪያ አገልግሎቶችን፣ የማህበራዊ ሚዲያ መድረኮችን፣ የድምጽ ማስተላለፊያ (ፖድካስት) አገልግሎቶችን እና የቀጥታ ስርጭት መድረኮችን ጨምሮ በኦንላይን መድረኮች ላይ ዲጂታል ይዘትን በመፍጠር እና በማሰራጨት የሚያገኘው ማንኛውም የገንዘብ ወይም በአይነት የሚገኝ ገቢ ነው። ይህም የሚከተሉትን ገቢዎች ያካትታል፦ ሀ) ማስታወቂያዎች እና ስፖንሰርሺፖች፣ ለ) የምርት ስም ስምምነቶች እና ድጋፎች፣ ሐ) የአጋርነት ግብይት እና የምርት ምደባዎች መ) የደጋፊዎች አስተዋጽኦ፣ የገንዘብ ስጦታዎች ወይም የብዙሃን የገንዘብ ማሰባሰብ (ክራውድ ፈንዲንግ)፣ ሠ) የአባልነት ክፍያዎች፤ ረ) የዲጂታል ወይም የአካላዊ ሸቀጦች ሽያጭ፣ ሰ) ለማስተዋወቂያ እንቅስቃሴ ምትክ የተገኙ ዕቃዎች ወይም አገልግሎቶች እና ሸ/ ከዚህ በላይ ከተጠቀሱት ጋር ተመሳሳይነት ያላቸው ሌሎች ክፍያዎች፡፡

September 1, 2026 2.4K 7