ለቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ አመራርና ሠራተኞች በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ተጠናቀቀ፡፡ ነሐሴ… — M.O.R. Medium Tax Payers No 1 Branch Office — TG.ME

ለቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ አመራርና ሠራተኞች በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ተጠናቀቀ፡፡

ነሐሴ 08/2018 ዓ/ም

በገቢዎች ሚኒስቴር የመካከለኛ ቁ.1 ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት አመራርና ሠራተኞች በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ ከነሐሴ 07/2018 ዓ/ም ጀምሮ ለሁለት ቀናት ያህል ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ተጠናቀቀ፡፡

የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የተቋማዊ አቅምና ድጋፍ ዘርፍ ም/ሥራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ አቡ ብርኪ ስልጠናውን በይፋ ባስጀመሩበት ወቅት ዕቅድ አለማቀድ እንደውድቀት እንደሚቆጠር ገልፀው ስራን በዕቅድ በመምራት ኢኮኖሚው የሚያመነጨውን ገቢ ለመስብሰብ ይህ ስልጠና ወሳኝ መሆኑን ጠቁመው በዚህ ስልጠና ላይ ለሚሳተፉ የቅ/ጽ/ቤቱ አመራርና ሠራተኞች ትኩረት ሰጥተው እንዲከታተሉ አሳስበዋል።

ስልጠናው በዕቅድና ሪፖርት አዘገጃጀት፣ በተቋሙ ራዕይ፣ ተልዕኮና እሴቶች፣ የትኩረት መስኮችና አቅጣጫዎች እንዲሁም ስትራቴጂያዊ ግቦች ምንነትና አቀራረጽ፣ በBSc ዕቅድ አዘገጃጀትና ውጤት ተኮር አሞላል/ምዘና/ ዙሪያ በቅ/ጽ/ቤቱ የዕቅድና በጀት አፈጻጸም ክትትል ቡድን አስተባባሪ በሆኑት በአቶ ሙሉጌታ አበባው አማካኝነት ተሰጥቷል።
August 14, 2026 8K