የሙያ ሥነ-ምግባርና የሀብት ምዝገባ ስልጠና ተሰጠ
………..
ነሐሴ 18/2018 ዓ.ም — የምስራቅ አዲስ አበባ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
የምስራቅ አዲስ አበባ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በአዲሱ የሴግመንቴሽን ምደባ ወደ ቅርንጫፉ ለተመደቡና በቅርብ ጊዜ በቅጥር ለተቀላቀሉ ሰራተኞች የሙያ ሥነ-ምግባርና የሀብት ምዝገባ ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና አዘጋጅቶ ሰጥቷል።
ስልጠናውን የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ሥራ አስኪያጅ ወ/ሮ ወርቅዓለም ተሾመ በመክፈት መልዕክት አስተላልፈዋል። ሥራ አስኪያጇ በመልዕክታቸው ተቋሙ እና ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የተሰጣቸውን የገቢ መሰብሰብ ተልዕኮ በተሳካ ሁኔታ ለመወጣት የሙያ ሥነ-ምግባር ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል።
እያንዳንዱ ሰራተኛም በተሰጠው የሥራ ኃላፊነት ላይ ሲሰራ አግባብነት ያላቸውን አዋጆች፣ ደንቦች፣ መመሪያዎችና የውስጥ አሰራሮች በመከተል ሥራዎችን በሙያዊ ሥነ-ምግባር መምራት እንደሚገባው አሳስበዋል።
በተጨማሪም ግብር ከፋዩ የሚሰጠውን አገልግሎት በእርካታ እንዲቀበል ለማድረግ የፍትሃዊነት፣ የተጠያቂነት፣ የታማኝነት፣ የግልጽነትና የአገልጋይነት መርሆች በሥራ ላይ መዋላቸውን ሙያተኛው በየጊዜው ራሱን መፈተሽ እንዳለበት አጽንዖት ሰጥተዋል።
በመድረኩ የተቋማዊ ስጋት ሥራ አመራርና ሥነ-ምግባር ቡድን አስተባባሪ ወ/ሮ ወላንሳ ወጋየሁ የገቢ ዕቅዱን በተሳካ ሁኔታ ለማሳካትና ሥራዎች በጥብቅ የሥራ ዲሲፕሊን እንዲመሩ የሚያግዙ መሰል ስልጠናዎች በቀጣይነት እንደሚሰጡ ገልጸዋል።
በስልጠናው የሥነ-ምግባር ጽንሰ-ሀሳብ፣ አስፈላጊነቱና የሙያ ሥነ-ምግባር በአቶ አዲሱ ኡርጌሳ፣ የሀብት ምዝገባ ጉዳይ ደግሞ በአቶ ጌታሰው አሰፋ በተግባራዊ ምሳሌዎች ተዳስሰዋል።
ይህ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የሰው ሀብት ሥራ አመራርና ልማት ሥራ ሂደት አስተባባሪነት የተዘጋጀ ሲሆን፣ ዓላማውም አዲስ የተቀላቀሉና በአዲሱ የሴግመንቴሽን ምደባ የተመደቡ ሰራተኞች ሙያዊ ኃላፊነታቸውን በሥነ-ምግባር፣ በተጠያቂነትና በተቋሙ አሰራር መሠረት እንዲወጡ ማጠናከር ነው።
“ሥነ-ምግባር የተጨማሪ ሥራ አይደለም፤ የሥራችን መሠረት ነው።”
5August 24, 2026 3.2K 2