M.O.R East Addis Ababa Branch: post #10222 — TG.ME

በታክስ ተገዢነት ክፍተት ከሚታይባቸው ግብር ከፋዮች ጋር ስልጠናና ውይይት ተካሄደ
……………
ምስራቅ አ.አ.አ.ግ.ከ.ቅ/ጽ/ቤት (ግንቦት 15/2018 ዓ.ም.)፦
የሀገርን ወጪ በሀገር ገቢ የመሸፈን ዓላማን በማሳካት የሀገር የልማት አውታሮችን ለማስፋትና እድገትን ለማፋጠን ግብርን በኃላፊነት ማሳወቅና መክፈል የሁሉም ዜጋ ኃላፊነት መሆኑን የምስራቅ አዲስ አበባ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የታክስ ኦፕሬሽን ምክትል ሥራ አስኪያጅ አቶ ማቲያስ አየለ ገለጹ።
ይህን የተናገሩት በዛሬው እለት በታክስ ተገዢነት ክፍተት ከሚታይባቸው ግብር ከፋዮች ጋር በተካሄደው የስልጠናና የውይይት መድረክ ላይ ነው።
ምክትል ሥራ አስኪያጁ አያይዘውም፣ ተቀራርቦ በመስራትና ለሚገጥሙ ችግሮች በጋራ መፍትሔ በመስጠት የግብር አሰባሰብ ሂደቱን ቀልጣፋ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል። ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቱ የሚያጋራቸውን የታክስ መረጃዎች ግብር ከፋዮች የማህበራዊ ሚዲያ ተከተዮች በመሆን እንዲከታተሉ፣ በሚሰጡ ተከታታይ ትምህርቶችና ስልጠናዎችም ወደተሻለ የታክስ ስርዓት መምጣት እንደሚቻል ገልጸዋል።
በተጨማሪም የታክስ ለውጥን በጊዜ ማሳወቅ፣ ማናቸውንም የግብር ሂደቶች በቴክኖሎጂ ማስደገፍ እና የኢ-ፔይመንት (e-payment) የክፍያ ስርዓትን መከተል እንደሚገባ አሳስበዋል። በተያዘው ወር የትርፍ ክፍፍል ግብር፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) እንዲሁም የሶስተኛው ሩብ ዓመት ቅድመ ክፍያ ማሳወቂያና መክፈያ ወቅት በመሆኑ፣ ግብር ከፋዮች ከወዲሁ ግብራቸውን በማሳወቅና በመክፈል ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።
በመድረኩ ላይ፦አቶ እሸቱ ኢራጎ (የታክስ ከፋዮች ትምህርትና መረጃ ከፍተኛ ባለሙያ)፦ ስለ አዲሱ የገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 1395/2017፤አቶ ብርሃኑ በላይ (የታክስ ከፋዮች ትምህርትና መረጃ ባለሙያ)፦ በታክስ ሕግ ተገዢነትና በኦዲት አሰራር ሂደት ዙሪያ፤ለተሳታፊዎች ስልጠና ሰጥተዋል::
❤14