M.O.R East Addis Ababa Branch: post #10226 — TG.ME

በነሀሴ ወር ሞጁላር ስልጠናቸውን ላጠናቀቁ ግብር ከፋዮች ጋር ውይይት ተካሄደ
………………
ምስራቅ አ/አ/አነ/ግ/ከ/ቅ/ጽ/ቤት ነሀሴ 25 /2018
ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ግብር ከፋዮች ታክስን በፈቃደኝነት እንዲከፍሉና ሀገራዊ ሀላፊነታቸውን እንዲወጡ ከሚያስችላቸው መንገዶች አንዱ ሞጁላር የተሰኘውን ስልጠና ለ90 ሰዓታት በመስጠት በታክስ ምንነትና አዋጅ ደንብ መመሪያና አሰራር ዙርያ ስልጠና እዲያገኙ ማድረግ ነው ፡፡
በዛሬውም እለት ሰልጣኝ ግብር ከፋዮች የመጨረሻውን ከፍል የሞጁላር ስልጠና በመውሰድ በትምህር አሰጣጥ ዙርያ ውይይት ከወ/ሮ የሺወርቅ ተጫኔ የታክስ ትምህርትና መረጃ አቅርቦት የስራ ሂደት አስተባባሪ ጋር አካሂደዋል ፡፡
ከዚህም ጋር ተያይዞ የታክስ አስተዳደራዊ እና የወንጀል ቅጣቶች ዙርያ ስልጠና የተሰጠ ሲሆን አቶ ውቡ ፋንታው የታክስ ትምህርት ከፍተኛ ባለሙያ ስልጠናውን ሰጥተዋል ፡፡
…….
👏3❤2👍1