Minber TV: post #24116 — TG.ME

ኸድር ታጁ ባለፉት ዓመታት ለግሉ ብቻ የተሠጠው በሚመስል የአጻጻፍ ሥልት ያለማቋረጥ የታሪክ መጽሐፍትን በማቅረብ ላይ የሚገኝ ጸሐፊ ነው፡፡ “ዓምደ ሀገር - ሸይኽ ዓሊ ጎንደር”፣ “ዳናዎቹ ቅጽ 1”፣ “ዳናዎቹ ቅጽ 2”፣ “ሸይኽ ሰይድ ኢብራሂም - የሸይኽ ጫሌ አንጸባራቂ ታሪክ”፣ “የበጌ ምድር አራጣ ሊቃውንት (ዑለማዎች)” እና “አግራሞታዊ ጉዞ” ከሥራዎቹ መካከል ይጠቀሳሉ፡፡ ከሰሞኑ ደግሞ በተያዘው ዓመት ጥቅምት 9/2018 ከምድር ሕይወት የተለዩትን የተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስን የሕይወት ታሪክ መጽሐፍ በማጠናቀቅ ለአንባቢያን ሊያደርስ መሆኑን አሳውቋል፡፡ የሚንበር ቲቪው አሕመድ ዓብዱረሕማን ስለ አዲሱ መጽሐፍ ላቀረበለት ጥያቄ ምላሹን በጽሑፍ ሰጥቷል፡፡ መልካም ንባብ፡-

ከቀናት በኋላ መስከረም 1/2018 በድጋሚ አገኘኋቸውና ቤታቸው በረንዳ፣ እርሳቸው በወንበር እኔ ወለል ላይ ተቀምጬ ጭውውት ጀመርኩ። በሕይወቴ ረዥም ሰዐት ያነጋገርኩት፣ ያዳመጥኩት፣ ያን ዕለት ነበር። እርሳቸውም አያሌ ውሐ ያልነካቸውን የሕይወት ፋናዎች፣ ገጽታና የታሪክ መረጃዎች በረዥም ሰዐታት ያካፈሉት ያን ጊዜ ይመስለኛል፤ ያለምንም ፋታ ቆይታችን 220 ደቂቃ ገደማ የፈጀ ነበር። ያን ዕለት ብዙ ስቀዋል፣ ብዙ አልቅሰዋል፣ ብዙም ተክዘዋል፤ ለእኔም ጎላ ብሎ የሚታወሰኝ ሆኖ አልፏል፡፡

ሙሉውን በድረ ገጽ ያንብቡ፦ https://minbertv.com/?p=11759
❤18🙏3
August 28, 2026 3.2K