#ነገ_እንገናኝ
ታሪክ የተጻፈው በቀለም ብቻ አይደለም
በሰዎች እምነት፣ ጉዞ፣ ትውስታና አሻራ ነው። ኢትዮጵያ በረጅሙ ታሪኳ ውስጥ ብዙ ታሪኮችን በውስጧ አምጣለች፤ ከእነዚህም መካከል የእስልምና ጉዞ የራሱ ልዩ አሻራ አለው።
“እስልምና በኢትዮጵያ ከቅድመ ክርስቶስ እስከ ዛሬ” ዓብዱልጀሊል ዓሊ ካሳ
መጽሐፉ ይህን ረጅም የታሪክ ጉዞ ከጥንት ዘመናት እስከ ዛሬ በመከተል እንድናነብ፣ እንድንጠይቅና እንድንመረምር ይጋብዘናል። ይህ የመጽሐፍ ውይይትም መጽሐፉን ለመዳሰስ ብቻ ሳይሆን፣ ታሪክን ከገፅ አውጥተን በጋራ ለመጠየቅና ለመረዳት የምንገናኝበት ይሆናል። የማናውቀውን ለማወቅ፣ የምናውቀውን በአዲስ ዓይን ለማየት እና ከትናንት ታሪክ ዛሬን ለመረዳት ለነገ ቀጠሮ እንያዝ!
🗓 ነገ ነሐሴ 17
🪧 ዋልያ መፅሐፍት መደብር ( 4 ኪሎ ኢኽላስ ህንፃ)
#ኑ_እንወያይ
#በንባብ_ወደ_ከፍታ
#ቅኝተ_መፅሐፍት


























