በሰሜን ኮሪያ ራስን ማጥፋት በሀገር ክህደት ሊያስቀጣ ነው❗️ በሰሜን ኮሪያ ራስን ማጥፋት በሶሻሊስት ሥርዓቱ… — Min Addis? — TG.ME

በሰሜን ኮሪያ ራስን ማጥፋት በሀገር ክህደት ሊያስቀጣ ነው❗️

በሰሜን ኮሪያ ራስን ማጥፋት በሶሻሊስት ሥርዓቱ ላይ የተፈጸመ የሀገር ክህደት ወንጀል ተደርጎ እንዲቀጣ የሚል መመሪያ በሀገሪቱ መሪ ኪም ጆንግ ኡን መተላለፉን ዓለም አቀፍ ሪፖርቶች ጠቁመዋል።

ይህ ያልተለመደ ውሳኔ የተላለፈው በሀገሪቱ ውስጥ ራስን የማጥፋት ድርጊት እየጨመረ በመምጣቱ ሲሆን፣ የአካባቢው ባለሥልጣናት በየክልላቸው መሰል ድርጊቶች እንዳይፈጸሙ መከላከል ካልቻሉ በግላቸው ተጠያቂ እንደሚሆኑ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል። ይሁን እንጂ ከሀገሪቱ የሚወጡ መረጃዎች ጥብቅ ቁጥጥር የሚደረግባቸው በመሆኑ፣ ይህ መመሪያ በሰሜን ኮሪያ መንግሥት በኩል በይፋ አልተረጋገጠም።

ይህ አዲስ ፖሊሲ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ትኩረትን የሳበ ሲሆን፣ በሰዎች የአእምሮ ጤና፣ በመንግሥት ቁጥጥር እና በሰብዓዊ መብቶች ዙሪያ ላይ አዲስ ክርክር አስነስቷል። ተቺዎች እና የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች እንደሚናገሩት ከሆነ፣ ድርጊቱን በሕግ መከልከል መንግሥት ሰዎችን ወደ ተስፋ መቁረጥ የሚገፉትን ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ከመፍታት ይልቅ፣ ለገጽታውና ለርዕዮተ ዓለሙ ብቻ እንደሚጨነቅ የሚያሳይ ነው ብለዋል።

(አዲስ አድማስ)
@min_ddis
❤10😁4👍3🤔1
July 18, 2026 3.1K 1