ተፈተዋል‼️
ቀሲስ በላይ መኮንን በአመክሮ ከእስር ተለቀቁ!
በሐሰተኛ ሰነድ ከአፍሪካ ኅብረት የባንክ ሒሳብ ከ6 ሚሊዮን ዶላር በላይ ለማዘዋወር ሞክረዋል በሚል የተከሰሱት ሊቀ አእላፍ ቀሲስ በላይ መኮንን በአመክሮ ዛሬ ከእስር ተለቀቁ።
ቀሲስ በላይ በመጀመሪያ የ5 ዓመት እስራትና 10 ሺሕ ብር ቅጣት ተወስኖባቸው ነበር። በኋላ ይግባኝ በማቅረባቸው ቅጣታቸው ወደ 3 ዓመትከ7 ወር ዝቅ ብሏል።
የእስር ጊዜያቸውን በማረሚያ ቤት ባሳዩት መልካም ሥነምግባር ምክንያት በአመክሮ እንዲለቀቁ መወሰኑ ታውቋል።
(የመረጃው ምንጭ ዘ-ሃበሻ ነው)
@min_ddis

13
3
3September 2, 2026 1K 1