ኢትዮጵያ ይዘት ፈጣሪያችን ተጠቃሚ የሚደረግ "ሲድሮ" የተሰኘ ኢትዮጵያዊ ቲክቶክ መተግበሪያ አፕልኬሽን ይፋ ተደረገ።
*
ኢንፍራን ቴክ ሶፍትዌርና ቴክኖሎጂ ስራንና ህይወትን ቀላል የሚደረግ አፕልኬሽንና ሶፍትዌሮችን አበልፃጎ ስራ ላይ በማዋል የሚታወቅ ድርጅት ሲሆን ከዚህም መካከል የብሔራዊ ባንክ፣የንግድ ባንክ፣የአዲስአበባ ትራፊክ ማኔጅመንት የዲጅታል ስርዓቶችን በማበልፀግ እና ስራ ላይ እንዲውል ያስቻለ የሶፍትዌርና የቴክኖሎጂ ድርጅት ነው።
ከዚሁም ጋር በተያያዘ ኢንፍራ ቴክ የሀገር ውስጥ የይዘት ፈጣሪዎችን በኢኮኖሚ ተጠቃሚ ለማድረግ እና የወጪ ምንዛሬ ወደ ሀገር ማሰገባት የሚስችል "ሲድሮ"የተሰኘ አዲስ የሶሻል ሚዲያ መተግበሪያ ወይም ኢትዮ ቲክቶክ በትላንትናው ዕለት ቦሌ በሚገኘው ስካይ ላይት ኢንተርናሽናል ሆቴል ይፋ አድርጓል ።
በዚህም ፕሮግራም ላይ የኩባንያው የስራ ኃላፊዎች ተዋቂ ግለሰቦች ተፅዕኖ ፈጣሪዎች እና የቴክኖሎጂ ባለሙያዎች ተገኝተዋል ።የኢንፍራ ቴክ መስራች እና ዋና ስራ አስፈፃሚ የሆኑት አቶ ቀዳማዊ ሙሉዓለም እንደገለፁት መተግበሪያው የሀገር ውስጥ የክፍያ አማራጮች ቴሌ ብር ቻፓ እና አለም አቀፍ አማራጮች በኩል ክፍያ የሚፈፀም እና ይህም በሀገር ውስጥ ያሉት ሆነ በወጪ ሀገር የሚኖሩ ዲያስፖራ አባለት ለይዘት ፈጣሪዎች በስጦታ በችሮታ መልክ ደጋፍ እንዲያደረጎ ያስችላል ተብሏል ። ከዚህም ሌላ አለም አቀፍ ሶሻል ሚዲያ ለምሳሌ ቴክቶክ ለሀገር ውስጥ ይዘት ፈጣሪዎች በሚሊዮን የሚቆጠር ተከታይ ቢኖራቸውም የክፍያ ስርዐቱ ባለመመቻቸቶ ያጋጥማቸው የነበረውን ክፍያ አለመገኘት ይፍታል ተብሏል ።
ይህ አፕ ሙሉ ለሙሉ በኢትዮጵያውያን የበለፀግ ሲሆን ዕድሜያቸው ከ18 አመት በላይ የሆኑ ሁሉ መጠቀም እንደሚችሉ በወቅቱ ተገልጿል ።
2
2
1September 1, 2026 1.9K 1