ከ300 ሚ. ዶላር በላይ የሚያወጡ ተሽከርካሪዎች በጂቡቲ ወደብ መታገዳቸው ተገለጸ! 👉አስመጪዎች ለከፍተኛ… — Min Addis? — TG.ME

ከ300 ሚ. ዶላር በላይ የሚያወጡ ተሽከርካሪዎች
በጂቡቲ ወደብ መታገዳቸው ተገለጸ!

👉አስመጪዎች ለከፍተኛ ኪሳራ ተዳርገናል አለ

በጂቡቲ ወደብ ከ8 ወራት በላይ ቆመው በሚገኙና ግምታቸው ከ300 ሚሊዮን ዶላር በላይ በሚሆኑ ከ4,500 በላይ የከባድ ጭነትና የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች ምክንያት፣ አስመጪዎች ለከፍተኛ ኪሳራ መዳረጋቸውን ሪፖርተር ጋዜጣ ዘግቧል። ተሽከርካሪዎቹ ወደ አገር እንዳይገቡ የታገዱት አገሪቱ በተፈጥሮ ጋዝ አጠቃቀም መመሪያ ምክንያት በቤንዚንና ናፍጣ የሚሠሩ ተሽከርካሪዎች እንዳይገቡ በወጣው አዲስ መመሪያ ነው። በመሆኑም ከ100 በላይ አስመጪዎች ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ደብዳቤ በማስገባት አስቸኳይ መፍትሔ እንዲሰጣቸው ተማፅነዋል።

እንደ ሪፖርተር ጋዜጣ ዘገባ፣ የጉምሩክ ኮሚሽንም ለችግሩ መፍትሔ እንዲሰጠው የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶችን በተደጋጋሚ ጠይቋል። መመሪያው ከመውጣቱ በፊት ተሽከርካሪዎቹን ያዘዙት አስመጪዎች በየቀኑ ለተጨማሪ የኪራይና የወደብ ወጪ እየተዳረጉ ይገኛሉ። በተጨማሪም እገዳው በመቀጠሉ ምክንያት መንግሥት ማግኘት የሚገባውን ከ1.8 ቢሊዮን ብር በላይ የታክስ ገቢ ያጣል ተብሏል።

(መረጃው የሪፖርተር ጋዜጣ ነው)
@min_ddis
❤1🤔1😢1
August 31, 2026 1.8K 1