'እርስዎን ሳይ ወላሂ አልፌ መሄድ አልቻልኩም!'❤🙌
ይሄ ሙስሊም ወጣት ልጅ አባን "ልሸኝዎት" ብሎ መኪናው ውስጥ ያስገባቸዋል። መንገድ እንደጀመሩ "ለወትሮዬ እናቶችን ነበር የምሸኘው፣ እርስዎን ሳይ ግን ወላሂ አልፌ መሄድ አልቻልኩም!" አላቸው።
አባም "እንዲህ ያለህ ማር የሆንክ ልጅ ከየት ተገኘህ?" ሲሉት "አላህአምዱላሂ" ደስ እያለኝ የማደርገው ነው፣ የሚሄዱበት ነው የማደርስዎ" እየተባባሉ ከጀሞ ሚካኤል ገላን አደረሳቸው።
ሊመለስ ሲል ስልኩን ወሰዱ እደውልልሀለሁ ወንድሜ አሉት፣ ሁሌም እጸልይልሀለሁ" አሉት እሱም "እሺ አባቲ እኔም እዘይሮታለሁ" ካላቸው በኋላ ወርደው ሄዱ።
ለዚህ ነው በወጣቶቻችን ተስፋ የማደርገው። ልጁን የምታውቁት ምርቃቴን አድርሱልኝ። የሚኮረጅ መልካም ስራህን አብዝተህ እንድትባረክበት ጤና እና እድሜ ይስጥህ በሉት!
(በፍፁም አጥናፈወርቅ)
@min_ddis

43
3
3
3July 17, 2026 3.1K 1