ትግራይ ክልል የ”አምባሳደር አሸንዳ” መዓረግ ነጠቀ
የትግራይ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ትናንት በሰጠው ይፋዊ መግለጫ፣ በ2017 ዓ.ም የ”አምባሳደር አሸንዳ” ውድድር አሸናፊ በመሆን ማዕረጉን ተቀብላ የነበረችው ወ/ት ዜማ እምብዛ ከተሰጣት የክብር ማዕርግ መነሳቷን አስታውቋል። ቢሮው ውሳኔውን ያስተላለፈው ግለሰቧ የተጣለባትን ባህላዊ ኃላፊነት ወደ ጎን በመተው ለሕዝቡ እሴትና ክብር የማይመጥኑ ተግባራትን ፈጽማለች በሚል ክስ ነው።
እንደ ቢሮው መግለጫ መነሻ ከሆነ፣ ወ/ት ዜማ እምብዛ ከዚህ ቀደም ለፈጸመቻቸው ተመሳሳይ ጥፋቶች በእድሜዋና በቤተሰባዊ ምክክር ታይቶ፣ ይፋዊ ይቅርታ እንድትጠይቅና እንድትታረም ዕድል ተሰጥቷት ነበር። ይሁን እንጂ የተሰጣትን ዕድል ከመጠቀም ይልቅ የአሸንዳ ባህልን የማስተዋወቅ ኃላፊነቷን ወደ ጎን በመተው፣ የአሸንዳ በዓልን “አሸንዳ ኢትዮጵያ” በሚል መጠሪያ የማስተዋወቅ ሥራ መጀመሯንና ይህ ተግባር ደግሞ የሕዝቡን ባህላዊ እሴቶች እንደማይወክል ቢሮው በክሱ ላይ አመልክቷል።
በዚህም ምክንያት የተጣለባትን ትልቅ አደራና ኃላፊነት ባለመወጣቷ እንዲሁም ከባህሉ መርሆዎች ውጪ በመንቀሳቀሷ፣ የተሰጣት የ”አምባሳደር አሸንዳ” ማዕርግ ከሐምሌ 9 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በይፋ መነጠቁን የትግራይ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ለሕዝብ ይፋ አድርጓል።
(Via:_ፋስት መረጃ)
@min_ddis

12
7
1
1July 16, 2026 2.7K