ቤተሰቦቹን ለመጠየቅ ትውልድ ቀየው የሄደው አትሌት በድንገት ህይወቱ አለፈ!❗️ ነፍስ ይማር🙏 አትሌት ጉሌቦ… — Min Addis? — TG.ME

ቤተሰቦቹን ለመጠየቅ ትውልድ ቀየው የሄደው አትሌት በድንገት ህይወቱ አለፈ!❗️
ነፍስ ይማር🙏

አትሌት ጉሌቦ ዱርሳይ (ራምቦ)
በሀገረ ሰላም ማሰልጠኛ ማዕከል የተገኘ በኋላም በሀዋሳ ከተማ፣ እና በንግድ ባንክ ክለብ የነበረ ህይወቱ እስካለፈበት ቀን ድረስ ደግሞ በኢትዮ ኤሌክትሪክ አትሌቲክስ ክለብ የነበረ ጠንካራ እና ብቃቱን በተደጋጋሚ ሲያሳይ የነበረ ወጣት አትሌት ነበረ!!

አትሌቱ ለዕረፍት ቤተሰቦቹን ለመጠየቅ ወደ ደቡብ ኦሞ ዞን፣ ሀና ወረዳ ባቀናበት ወቅት በድንገት ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱ ቤተሰቡን፣ እና የአትሌትክስ ቤተሰቡን አሳዝኗል።
ለሟች ቤተሰቦች፣ ወዳጅ ዘመዶች እንዲሁም ለመላው የአትሌቲክስ ቤተሰብ መጽናናትን እየተመኘን
የአትሌት ጉሌቦ ዱርሳይ (ራምቦ) ህልፈተ ህይወት አስመልክቶ አዲስ ነገር ካለ መረጃው እንደደረሰን እናቀርባለን!!
ነፍስ ይማር!!
(Via:-EthioRunners)
@min_ddis
💔16❤4😢1😭1
July 16, 2026 2.9K