ከሩሲያ ጥቃት ቢሰነዘርስ ? የሚለው ዋና ስጋታቸው መሆኑንም #EL_PAIS በዘገባው ተመልክቷል።
"እየጨመረ ከመጣው የተፈጥሮ አደጋዎች እና - ከዩናይትድ ስቴትስ የደህንነት ከለላን የማጣት ስጋት - ካልተረጋጋው የጂኦፖለቲካዊ ሁኔታ - ከጦር መሳሪያ ፉክክር እና ከምንም በላይ ሩሲያን ከመስጋት ጋር በተያያዘ የአውሮፓ ህብረት ነዋሪዎች ለጦርነት ፣ ለሳይበር ጥቃቶች ፣ ለአዲስ የበሽታ ወረርሽኝ እና የአየር ንብረት ቀውስ መዘዞች መዘጋጀት አለባቸው"ሲሉ የአውሮፓ ባለስልጣናት አሳስበዋል።
ለእነዚህ አደጋዎች ምላሽ ለመስጠት ሲባል ለሁሉም የህብረቱ ዜጎች የውሃ አቅርቦት ፣ መድሃኒት ፣ ባትሪዎች እና ቢያንስ ቢያንስ ለ72 ሰዓታት የሚያቆይ በቂ ምግብ እንዲያዘጋጁ የአውሮፓ ህብረት (ብራሰልስ)ጥሪ አቅርቧል።
ይህም ዛሬ ረቡዕ በይፋ ከሚቀርበው የአውሮፓ ህብረት የዝግጁነት ስትራቴጂ ውስጥ አንዱ ነው ተብሏል።
"አንድ ወይም ከዚያ በላይ የሆኑ አባል ሀገራት ለሚሰነዘሩ የትጥቅ ጥቃቶችን ጨምሮ ለትላልቅ ክስተቶች እና ቀውሶች ዝግጁ መሆን አለብን - ይህ ለወደፊቱ የአውሮፓ ዝግጁነት እና የትጥቅ ጥቃትን የመቋቋም ችሎታችንን ለመፈተን ይውላል።"ሲሉ ባለስልጣናቱ ለህትመቱ ተናግረዋል።
@MayalInfoWorld