የብሪታኒያ ዜግነት ያለው ቅጥረኛ ወታደር በሩሲያ በሽብርተኝነት ተከስሶ የ19 ዓመታት እስር ተፈረደበት !
ጀምስ ስኮት ራይስ አንደርሰን የተባለው ይህ የብሪታኒያ ዜጋ ከኪየቭ ኃይሎች ጋር በመወገን ሩሲያን ሲወጋ መቆየቱ ተረጋግጦ በኩርስክ በሚገኘው 2ኛ የምዕራባዊ ወረዳ ወታደራዊ ፍርድ ቤት የ19 ዓመታት እስራት ተፈርዶበታል።
የኩርስክ ክልል የፍትህ ስርዓት ለ - የተባበሩት ፕሬስ አገልግሎት እንደገለጸው አንደርሰን በሩሲያ የሽብርተኝነት ህግ እና "በቅጥረኛ ነፍሰ ገዳይነት" የተከሰሰው በህገ ወጥ መንገድ ወደ ኩርስክ ክልል ገብቶ ጥቃት ከፈጸመ በኋላ ነው።
ፍርድ ቤቱ አንደርሰን የመጀመሪያውን 5 የቅጣት ዓመታት በእስር ቤት እንዲጨርስ ወስኖ ቀሪውን የቅጣት ጊዜ ደሞ በግዛት ውስጥ ሆኖ ለማህበራዊ ግልጋሎት የሚሆን ስራን ያለ አገዳች ክፍያ እየሰራ የቅጣት ጊዜውን እንዲጨርስ ውሳኔውን አፅድቋል።
video = #TASS
@MayalInfoWorld
14
3March 23, 2025 1.1K 2