መረዳት ከመውደድ ይበልጣል፤ የማይረዳህ ሰው እንዴት ሊወድህ እንደሚችል አያውቅም።
እውነቱን ለመናገር መውደድ ቀላል ነው፤ “እወድሃለሁ” ማለት ማንም ይችላል። ግን እውነተኛው ፈተና መረዳት ላይ ነው። ማንነትህን፣ ድካምህን፣ በዝምታ የምትታገለውን ጦርነት፣ እና የራስህን ባህሪ በትክክል ሳይረዳ “እወድሃለሁ” የሚልህ ሰው… በእውነቱ የሚወደው አንተን ሳይሆን በአእምሮው ውስጥ የፈጠረውን ያንተን ምስል ነው።
መረዳት ከሌለ ፍቅር ውስብስብ ይሆናል፤ አንዳንዴም ያስጨንቃል። ግን አንድ ሰው በእውነት ሲረዳህ፣ የውስጥ ሰላም ታገኛለህ፤ እውነተኛ ምቾት ይሰማሃል።
ስለዚህ በህይወታችን “እወድሃለሁ” ከሚሉን ሰዎች ይልቅ “አውቅሃለሁ፣ እረዳሃለሁ” የሚሉን እውነተኛ ሰዎችን አላህ ያብዛልን።🤍
4
3June 30, 2026 1.4K 21