በዛሬው የሐዲስ እና ሱና መግቢያ ትምህርታችን፣ ሱናን የማይቀበሉ አካላት (ቁርኣኒዮች) የሚያነሷቸውን ውዥንብሮች ማጋለጣችንን እንቀጥላለን። እስልምና ሐዲስን ከተዛባ ትርጉም እና ከውሸት ለመጠበቅ የተጠቀመበት ጥበብ በየትኛውም የዓለም እና የሌሎች ሀይማኖቶች ታሪክ ታይቶ አይታወቅም።
በክፍሉ ውስጥ ትልልቅ የሐዲስ ሳይንሶች ተብራርተዋል፤ ከእነዚህም ውስጥ የትረካ ሰንሰለት (ሰነድ/ኢስናድ)፣ የዘጋቢዎችን ማንነትና ታማኝነት በጥልቀት ማጥናት (አል-ጀርሕ ወት-ተዕዲል)፣ የሐዲስን ድብቅ ችግሮች መመርመር (ዒልሙል ዒለል) እና የሐዲስን ጽሑፍ (መትኑን) ከቁርኣን ጋር ማመዛዘን (ዒልሙል ሙቱን) ይገኙበታል።
በተጨማሪም "ሐዲስ የተጻፈው ከ200 ዓመታት በኋላ ነው" የሚለው የሀሰት ክስ ውድቅ የተደረገ ሲሆን፣ ገና በነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ዘመን እና በሰሓባዎች ጊዜ (እንደ አብዱላህ ኢብኑ አምር፣ አቡ ሁረይራ እና አነስ ኢብኑ ማሊክ ባሉ ሰሀባዎች) ሐዲሶች ይጻፉ እና ይጠኑ እንደነበር በግልጽ ተብራርቷል። ዑመር ኢብኑ አብዱልአዚዝም ሐዲስ በይፋ እንዲሰባሰብ ትልቅ ሚና ተጫውተዋል። ሙሉ ትምህርቱን ይከታተሉ፦
https://t.me/Hidayaic8212















