ሱናን እና ሐዲስን ውድቅ የማድረግ አዝማሚያ በታሪክ መቼ እና እንዴት ተጀመረ?
ሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል በወንድማችን ኢሊያህ ማህሙድ አማካኝነት እያቀረበ ባለው "የሐዲስ እና ሱና መግቢያ" የትምህርት ኮርስ፣ የዛሬው ትምህርት እጅግ ጠቃሚ የሆኑ እውቀቶችን አካትቷል። በዚህ ክፍል ሱናን እና ሐዲስን አለመቀበል በታሪክ መቼ እና በነማን እንደተጀመረ፣ እንደ ሙዕተዚላ እና ኸዋሪጅ ያሉ ቡድኖች አቋም፣ እንዲሁም በ19ኛው ክፍለ ዘመን በእንግሊዝ ቅኝ ግዛት ወቅት በህንድ የተነሱት "ቁርኣኒዮች" (ቁርኣን ብቻ ይበቃናል የሚሉ) እንቅስቃሴ አመጣጥ በሰፊው ተብራርቷል።
እነዚህ አካላት ሱናን ውድቅ በማድረጋቸው ምክንያት፣ ቁርኣንን በአረብኛ ቋንቋ ፍቺ ብቻ በመተርጎም እንደ ሶላት፣ ጾም፣ ሐጅ እና ዘካ ያሉ መሰረታዊ የዲን ትእዛዛትን እንዴት እንዳዛቡ ትምህርቱ በግልጽ ያሳያል። ይህን ወሳኝ ትምህርት በማዳመጥ በዲናችን ላይ ያለንን ግንዛቤ እናጠንክር።
https://t.me/Hidayaic8212
5
4September 16, 2026 293 6