ኢምፖርት ቀላል ሥራ አይደለም:: ሳይንስና አርት አለው:: ስልጠና ብቻ አይበቃውም:: ገብቶ መዋኘት እና የዕለት ተለት ክትትል, ያልተቋረጠ ውይይት እና መረጃ ስብ70 ይፈልጋል:: አንተ ሙሉ ያለቀለት የምሳ እቃ ወይም ቦርሳ ስንት እንደሚፈጅ ሒሳብ ሠርተኸው ትርፉ ትንሽ ይሆንብሃል ወይም አያዋጣህም:: ሥራው ውስጥ ስትገባ ግን ሽፋኑን ለብቻ, ገበሩን ለብቻ, ማንገቻውን ለብቻ የሚጭነው የቀደመው ኢምፖርተር ይበላሃል:: እንዴት እንደሚያዋጣቸው ግራ ይገባሃል:: ለየብቻ ሲጭኑት ቀረጡን ከ30% ወደ 5% በማውረድ ይሆናል ሳይንስና አርቱ:: አንተ ደግሞ ጥናትህን አጠናክረህ ገብተህ ገፍትረህ ልታስወጣው ትችላለህ:: ኢምፖርት ለማድረግ ዲክቴተር የግድ ይፈልጋል:: ዲክቴተሩ ወይ ጓደኛህ ወይ ብርቱ ዘመድህ ሊሆን ይችላል:: ምክንያቱም ከ A ጀምሮ Z ለመድረስ ቀላል አይደለም:: ዛሬ የጫንከው ዕቃ ሰነዱን እስከ አስር ዐመት መያዝ ይጠበቅብሃል:: የክፍያን part ብንወስድ አንድ ዕቃ ከጂቡቲ ለመግዛት "ሄሎ በቃ ጫነው" አይሠራም:: ግብይቱ በዶላር ነው:: ዶላሩ ደግሞ የኒውዮርክ ነው:: ልክ እንደ Etswitch ክፍያ ማቀባበያ SWIFT ሰርቨር ወይም መሥሪያ ቤት ደግሞ ቤልጂየም በመሆኑ ይህንን ዙሪያ ጥምጥም ለማወቅ ስልጠና የግድ ይላል:: ኢትዮጵያም ቡና ሽጣ ያገኘችውን ዶላር ለቦርሳ ማንገቻ ወይም ሰንኬሎ ዝም ብላ አትሰጥህም::
-> ስልጠናውን ለመመዝገብ
ወደ ምሥራቅ ማለቴ ስር ተመልከቱ 👇🏼👇🏼
10
9
1September 4, 2026 2.1K 9