በጾምና በስግደት እንኳ ይገኝ ይሆን? የሚያስብልን ውድ ዕቃ ማለትም ጀነት በመሰ^ዳደብ የሚፈልግ ሰው ድፍረት… — Hasen Injamo — TG.ME

በጾምና በስግደት እንኳ ይገኝ ይሆን? የሚያስብልን ውድ ዕቃ ማለትም ጀነት በመሰ^ዳደብ የሚፈልግ ሰው ድፍረት ይገርማል:: እርስበእርስ ይቅርና ከሌሎች ኃይማኖቶች ጋር ሳይቀር ጥንቃቄ ይጠይቃል:: ሙስሊሞች የክርስቲያኖችን ነገር በመስደ^ብ ሊያሰልሙ እንደማይችሉ ሁሉ አንዳንድ ክርስቲያኖችም ነቢ ሙሐመድን صلى الله عليه وسلم በመስ^ደብ ልንጠመቅ የሚጠብቁ አሉ:: እንደውም ይብስ እልህ ውስጥ ነው የሚከተው:: ስ^ድድብ ከዕውቀት ማነስ ነው የሚመነጨው:::

አንድ ምሳሌ ላንሳ:- ክርስቲያኖች ታቦት ይሸከማሉ:: ጦ^ር ሜዳም ሳይቀር ይዘው የሚሄዱባቸው አጋጣሚዎች አሉ:: ይህንን የሚተች ሙስሊም አይጠፋም:: ነቢ ዳውድ عليه السلام እና ጧሉት (ሳዖል) ታቦት ተሸክመው ጃሉትን (ጎሊያድን) ሊገጥሙ የሄዱበት ታሪክ በቁርኣን አለ:: ክርስቲያኖች ከዚያ ጀምሮ ይዘውት የመጡት ተግባር ነው የሚሆነው:: በጊዜ ርዝመት መሠረቱ ይልቀቅ አይልቀቅ ለሌላ ጥናት ቢተውም ግን መነሻ አለው:: "ታቡት" የሚለው ቃል ቁርኣን ውስጥ አለ:: ለያውም መላኢካዎች ናቸው ተሸክመው ያመጡት:: ታቡቱ ውስጥ የነቢያት ቅርሶች ነበሩበት:: ያንን ያዩ ጊዜ ልባቸው ተረጋጋ:: ጃሉትን ገጠሙና በጠጠር ረቱት ይላል ቁርኣን:: ይህንን ያመጣሁት ማወቅ ያሉብን በርካታ ነገሮች አሉ:: ባወቅን ቁጥር ልባችን ይረጋጋል:: ከስ^ድድብ እንወጣለን::
❤38👍4👏1
August 23, 2026 3.9K 5