ቃይስ ቢን አል-መሉህ ለይላ ከተባለች ሴት እብድ ያለ ፍቅር❤️ ይዞታል። እና በመስኪድ ውስጥ ወደ ሴቶች… — 𝐇𝐚𝐟𝐮 𝐢𝐬𝐥𝐚𝐦𝐢𝐜 𝐩𝐨𝐬𝐭™🕋 — TG.ME

✨✨✨✨✨✨✨✨✨

ቃይስ ቢን አል-መሉህ ለይላ ከተባለች ሴት እብድ ያለ ፍቅር
❤️ ይዞታል። እና በመስኪድ ውስጥ ወደ ሴቶች መስገጃ ስትሄድ ተከትሏት መራመድ ጀመረ። እና የት እንዳለ ሳያስተውል ሰዎች በተሰበሰቡበት በሰላት መስከጃ ተረማምዶ አለፈ። በድጋሚ በዛው መንገድ በአጠገባቸው አለፈ። ይህን የተመለከቱት ሰጋጆች እንዲህ አሉት፦

"እኛ በምንጸልይበት ጊዜ አስሬ አትመላለስ፤ ወይ ለምን ከእኛ ጋር አትጸልይም?"

እሱም፡-"እየጸለያችሁ ነበር እንዴ?"

እነሱም፦"አዎ እየሰገድንም እየጸለይንም ነበር!"

ይሄን ሲሰማ እንዲህ አላቸው፡-

"የእውነቴን ነው በአላህ እምላለሁ አላየኋችሁም!።
የእውነቴን ነው እኔ ለይላን እንደ ወደድኳት እናንተ አላህን ብትወዱ ኖሮ
ጭራሽም ባላያችሁኝ ነበር.."
🙁

🤩hafu_post
🔥26👍15❤9
September 5, 2026 1.2K 11 7