የበረሃ እንባ 💔 {የሊቢያ በርሃ } ፀሐፊ zoya~ ክፍል 2 .......ሌሊቱ ሊነጋ የሰዓታት ዕድሜ ብቻ… — 𝐇𝐚𝐟𝐮 𝐢𝐬𝐥𝐚𝐦𝐢𝐜 𝐩𝐨𝐬𝐭™🕋 — TG.ME

የበረሃ እንባ 💔    {የሊቢያ በርሃ }

ፀሐፊ zoya~


ክፍል 2

.......ሌሊቱ ሊነጋ የሰዓታት ዕድሜ ብቻ ቀርተውታል የኦርሳም ትከሻ የለበሰው ቲሸርት በላብ ረስርሶ ሰውነቱ ላይ ተጣብቋል እያንዳንዱ የዱቄት ኩንታል በትከሻው ላይ ሲያርፍ የአከርካሪው አጥንት እሪ የሚል ይመስለዋል ግን አልቆመም ሀኪያ... እ ማ... እያለ በልቡ ይደጋግማል  የነሱ ረሃብና ህመም ከኩንታሉ በላይ ከብዶታል።
​"ኦሪ  መጨረሻው ነው በርታ!"

ኢዘዲን  የዱቄት አቧራ የለበሰ ፊቱን በሸሚዙ እጅ እየጠረገ ጮኸ።
​የመጨረሻዋን ኩንታል ጭነው ሲያበቁ ኦርሳም እዛው መሬት ላይ ዘፍ አለ ሳንባው አየር አጥሮት ትንፋሹ ቁርጥ ቁርጥ ይላል። ሹፌሩ አቶ በቀለ ከመኪናው ወርዶ ወደ እነሱ መጣ። የቆሸሸውን ቦርሳውን ከፍቶ ጥቂት የቆሸሹ ብሮች መዘዘ።

​"ጎበዞች ናችሁ። ይሄው የድካማችሁ..."
እያለ ለእያንዳንዳቸው ዘረጋላቸው።
​ኦርሳም ብሩን ሲቀበል እጆቹ ይንቀጠቀጣሉ ህይወቱን ሙሉ የናፈቀው ያህል በጉጉት እያየው ይቺ ብር የሀኪያ መድኃኒት ናት ይቺ ብር የቤቱ የሳምንት ቀለብ ናት።

​ከኢዘዲን ጋር ወደ ቤት እየተመለሱ ሳለ መንገዱ ወጋገን መታየት ጀምሯል
"ኢዙ... አመሰግናለሁ" አለው ኦርሳም ድምፁ እየተቆራረጠ።
ኢዘዲን ግን ቆም አለና ኦርሳምን በትኩረት አየው። "ኦሪ... ይሄ ስራ እስከመቼ ነው? ዛሬ የሀኪያን መድኃኒት ትገዛለህ ነገስ? ከነገ ወዲያስ? ሁሌም እንዲህ ኩንታል ተሸክመን እናረጃለን?

​ኦርሳም ዝም አለ ጥያቄው አዲስ ባይሆንም መልሱ ግን ሁሌም የጠፋበት እንቆቅልሽ ነው።
"ታዲያ ምን ይደረግ? ባዶ እጄን ከመቀመጥ...

ኢዘዲን ትከሻውን ቸብ አደረገውና ፈገግ ለማለት እየሞከረ
"አይዞህ ኦሪ... ቢያንስ ዛሬ እጅህ ላይ የድካምህ አለች ይቺን ይዘህ ገብተህ ማዘሯን ና ሀኪያ ማስደሰት ትልቅ ነገር ነው" አለው።
​ኦርሳም ቀና ብሎ ወደ ሰማዩ ተመለከተ። "አዎ ኢዙ... ዋናው ነገር ያ ነው። ግን መቼ ነው እኛም እንደሌሎቹ በልተን ጠግበን፣ ተኝተን የምናድረው? ሁልጊዜ ይሄ ለሊት መከራችንን የሚያሳይ ሳይሆን፣ ደስታችንን የሚያበስር የሚሆነው መቼ ነው?"

​ኢዘዲን ትንሽ አሰበና
"አላህ ያውቃል ብሮ ምናልባት ነገ ደግሞ የተሻለ ነገር ይዞ ይመጣ ይሆናል። ዛሬ ግን ይሄን አቧራ አራግፈን በሰው አይን ሳንገባ ሰፈር መድረስ አለብን አይመስልህም " አለው።

​ሁለቱም  በዝምታ ጥቂት ተጓዙ የጠዋቱ አየር ብርዱን እየጨመረ ቢመጣም በድካም የዛለው ሰውነታቸው ግን አይሰማውም ነበር። ሰፈሩ ጋ ሲደርሱ የጥበቃ ውሾች ጩኸትና የፈረሰኞች ኮቴ መሰማት ጀምሯል።
​"በቃ ኦሪ... በዚህ ልቀየስ " አለ ኢዘዲን ወደ ሰፈሩ መታጠፊያ ሲደርስ "ዛሬ ትንሽ እረፍት አድርግ። እኔም ወደ ቤት ሄጄ ልጋደም። ማታ ደግሞ መጋዘኑ ጋ ስራ ካለ እንገናኛለን"

​ኦርሳም "እሺ ኢዙ... አመሰግናለሁ ባንተ ነው ይሄ ሁሉ ። ለሊቱ ቢከብድም ብቻዬን ስላልሆንኩ ደስ ብሎኛል" አለው።
​ኢዘዲን እጁን ምስጋና እንደ ማያስፈልግ እየነገረው ወደ ቤቱ ሄደ ። ኦርሳምም ወደ ዝገቱ የቆርቆሮ በር እያመራ  ኪሱ ያለችውን ብር እንደገና ደባበሳት ድካሙ ሁሉ በደስታ ተቀየረ የቤቱን በር በቀስታ ገፋ አድርጎ ሲገባ እናቱ ኩሽና ውስጥ  አብርተው ሻይ ሊያፈሉ ሲዘጋጁ አገኛቸው።

​"ልጄ... መጣህ?" አሉት በስስት

​ኦርሳም ፈገግ ብሎ "መጣሁ እማ... " አላቸው።

የድካም ድምፁን ለመደበቅ እየሞከረ። የያዛትን ብር አውጥቶ እናቱ እጅ ላይ ሲያስቀምጥ እናቱ ብሯን ተመልክተው አይናቸው በእንባ ተሞላ። የትናንቱ ንዴትና ተስፋ መቁረጥ ጠፍቶ በጸጸት ስሜት ግንባሩን ሳም አደረጉት።
​"አላህ ይባርክልህ ልጄ አይዞህ...  ቅድም ተናድጄ ነው እኮ " አሉት። ኦርሳም ግን ምንም አልተናገረም ዝም ብሎ ወደ ሀኪያ የተናችበት ፍራሽ ሄዶ ቁጭ አለ ሀኪያ በሳል ብዛት ዝላ ተኝታለች የገዛላትን መድኃኒት ከጎኗ አስቀምጦ የቆሸሸውን ልብሱን ሳይቀይር ትኩር ብሎ አያት
​"ሀኩ ..." አላት በቀስታ።
​አይኖቿን በግማሽ ገልጣ አየችውና ፈገግ ለማለት ሞከረች። "ኦሪ... መጣህ? ሻይ ጠጣህ?"

​"አዎ ጠጥቻለሁ የኔ አሳቢ አጎሳቆልኩሻ ላንቺ አልበቃሁም ይቅር በይኝ እሺ አሁን አንቺ ብቻ ይሄን መድኃኒት ዋጪና ተኚ" አላት። ውስጡ ግን "ይቺ ብር ለስንት ቀን ትበቃናለች?" የሚለው ጥያቄ እንደ መርፌ ይወጋዋል። የዛሬዋ መድኃኒት ተገዛች የነገው የቤት ኪራይስ የሳምንቱ ቀለብስ?
​ቀኑን ሙሉ እንቅልፍ ሊወስደው አልቻለም።

የዱቄት ኩንታሉ በትከሻው ላይ ያሳረፈው ቁስል ይለበልበዋል። ትናንት ሌሊት አብሮት የነበረው ኢዘዲን የተናገረው ቃል በአእምሮው ይመላለሳል።

"ሁሌም እንዲህ ኩንታል ተሸክመን እናረጃለን?"

​ምሽት ላይ እንደገና ወደ መጋዘኑ ሄደ ዛሬ ግን እንደ ትናንቱ ስራ አልነበረም መጋዘኑ ተቆልፏል አካባቢው ጭር ብሏል ጥቂት ወጣቶች በረንዳ ላይ ተቀምጠው በዝምታ መሬት መሬት ያያሉ።

​"ዛሬ መኪና የለም?" ሲል ጠየቀ ኦርሳም አንዱን።

​"የለም... እስከ ሳምንቱ መጨረሻ አይመጣም ተብሏል" አለው ልጁ በደረቀ ድምፅ።

​ኦርሳም ተስፋ በመቁረጥ እዛው ድንጋይ ላይ ተቀመጠ። ኪሱ ባዶ ነው ትናንት ያመጣው ብር ለመድኃኒትና ለጥቂት አስቤዛ አልቋል። ኢዘዲን ከጨለማው ውስጥ ብቅ አለ። ፊቱ ላይ ትናንት የነበረው የድካም መንፈስ ሳይሆን ሌላ አይነት ቁርጠኝነት ይታያል።
​"ኦሪ... አየኸው አይደል? ዛሬ ስራ የለም። ነገም ላይኖር ይችላል። እህትህ ደግሞ ነገም መድኃኒት ትፈልጋለች" አለው ኢዘዲን አጠገቡ እየተቀመጠ።
​ኦርሳም ራሱን በእጆቹ ደገፈ።

"ታዲያ ምን ላድርግ ኢዙ? የት ልሂድ? መስረቅ አልችልም መለመን ደግሞ አይሆንም እሞታታለው እንጂ "
​ኢዘዲን ዙሪያውን አማትሮ ካየ በኋላ ድምፁን ዝቅ አድርጎ እንዲህ አለው "ስማ... ቅድም የሆነ ሰው አግኝቼ ነበር።እና የሆነ ነገር አማክሮኝ ነበር ስደት እንድንሞክር መክፈል ባንችልም መንገድ ላይ እየሰራን እንድንሄድ ሊያመቻችልን ይችላል። ይሄን እድል ካመለጠን እድሜ ልካችንን እዚህ መጋዘን ደጅ ስንጠባበቅ እናረጃለን"
​ኦርሳም ልቡ ክፉኛ ይመታል መሄድና መቅረት ተስፋና ስጋት ውስጡን ይናጡት ጀመር። ወደ ቤቱ ተመልሶ የእናቱን የዛለ ፊት ማየት አልፈለገም የሀኪያን ሳል መስማት ደግሞ አቅም አሳጥቶታል።
​"በቃ... መሄድ አለብኝ" አለ ኦርሳም ለራሱ በሹክሹክታ። ግን ጉዞው ወዴት እንደሆነ ምን እንደሚጠብቀው ገና አላወቀም ነበር
ቃሉ ሲናገር ድምፁ ከራሱ አልፎ ለኢዘዲንም በቅጡ አልተሰማውም ነበር። በቃላት ሊገልጹት የማይችሉት የከበደ ዝምታ በመካከላቸው ነገሰ።

​ኢዘዲን የኦርሳምን ውሳኔ ሲሰማ በረጅሙ ተነፈሰ እና "ቆራጥ መሆን አለብህ ኦሪ! ይሄ ለቤተሰቦችህ ስትል የምትከፍለው መስዋዕትነት ነው። ዛሬ ሌሊት 9 ሰዓት ላይ እዚሁ መጋዘን ጀርባ እንገናኝ። ልብስና የምታስፈልግህን ጥቂት ነገር ብቻ ያዝ። ለማንም እንዳትናገር... እናትህ ከሰሙ አያስኬዱህም" አለው።

​ኦርሳም ወደ ቤት እየተመለሰ መንገዱ ሁሉ ባዶ መስሎ ታየው። ሰፈሩን የቆርቆሮ ቤቶቹን ያደገበትን አቧራማ መንገድ በመጨረሻው አይን ተመለከታቸው ልቡ በሀዘን ይደማል። "እንዴት ሳልሰናበታቸው እሄዳለሁ?" የሚለው ሃሳብ ሊያሳብደው ደረሰ።
​ቤት ሲገባ እናቱ ኩሽና ውስጥ ቁጭ ብለው እየጠበቁት ነበር።

ክፍል ሁለት.. 2   ከ 100👍  ľįķę ቡሃላ ይቀጥላል......
❤84👍9💔5🍓1
August 29, 2026 2.4K 13