✨ᴅᴀɪʟʏ ʜᴀᴅɪᴛʜ✨
❴Part 259❵ #hadith259
"ነቢዩ (ሶ.ዐ.ወ) ተከታዩን ሲናገሩ ማድመጣቸውንአቡ ሁረይራ (ረ.ዐ) አስተላልፈዋል፡- "ከበኒ ኢስራኢሎችመካከል ሦስት ሰዎች -አንደኛው ለምፃም፥ ሌላኛው ራሰ-በራ፥ ሦስተኛው ደግሞ ዓይነ-ስውር- አሏህ ሊፈትናቸውፈለገ፡፡ መልአክ ላከባቸው፡፡ ለምፅ ያለበትን ሰው መጣና፡-"በጣም የምትወደው ነገር ምንድን ነው?" ሲል ጠየቀው፡፡"መልካም መልክና መልካም ቆዳ፡፡ ሰዎች እኔንእንዲጠየፉኝ ምክኒያት የሆነው በሽታዬምእንዲወገድልኝ" ሲል መለሰ፡፡ አበሰው -መላኢካው-፡፡አፀያፊው ሁኔታም ተወገደለት፡፡ መልካም መልክ ተሰጠ፡፡"ከገንዘብ የትኛው ነው ካንተ ዘንድ ይበልጥ ተወዳጅ?"በማለት ጠየቀው፡፡ "ግመል -ወይም ላም-" መለሰለት፡፡እርጉዝም ግመል ተሰጠው፡፡ "አሏህ ይባርክልህ" ሲልምመረቀው፡፡ ወደ ራሰ-በራው ሰውዬ በመሄድም፡- "እጅግ!ገፅ65የምትወደው ነገር ምንድን ነው?" አለው፡፡ "መልካምፀጉር፥ ሰዎች እንዲፀየፉኝ ምክኒያት የሆነው ራስ-በራዬም እንዲወገድ" አለ፡፡ አበሰው፡፡ በራው ተወገደለት፡፡ማራኪ ፀጉርም ተሰጠው፡፡ "ከገንዘብ የትኛው ነው ካንተዘንድ ይበልጥ ተወዳጅ?" ሲልም ጠየቀው፡፡ "ላም" አለ፡፡ያረገዘች ላም ተሰጠው፡፡ "አሏህ ይባርክልህ" አለው፡፡ ወደዓይነ-ስውሩ ዘንድ በመምጣት "ይበልጥ የምትወደውነገር ምንድን ነው?" ሲል ጠየቀው፡፡ "አሏህ የዓይኔንብርሃን መልሶልኝ ሰዎችን መመልከት መቻል" በማለትመለሰለት፡፡ አበሰው፡፡ አሏህ የዓይኑን ብርሃን መለሰለት፡፡"ከገንዘብ የትኛውን ነው ይበልጥ የምትወደው?" ሲልምጠየቀው፡፡ "ፍየል" አለ፡፡ ወላድ የሆነች ፍየል ተሰጠው፡፡ሁሉም ተራብቡ፥ ተበራከቱ፡፡ አንደኛው የአንድ ሸለቆግመል፥ ሌላኛው የአንድ ሸለቆ ከብት፥ ሦስተኛው ደግሞየአንድ ሸለቆ ፍየል ባለሃብቶች ሆኑ፡፡ በሌላ ወቅትመልአኩ ድሮ በነበረው መልክና አኳኋን ሆኖ ለምጻም ወደነበረው ሰው መጣና፡- "ችግር የደረሰብኝ መንገደኛ ነኝ፡፡አሏህና አንተ ከምትለግሱኝ ነገር በስተቀር ጉዞዬንለመቀጠል የሚያስችለኝ ስንቅ የለኝም፡፡ ለመዳረሻዬየሚሆነኝ ስንቅ ታቀብለኝ ዘንድ መልካም መልክ፥ መልካምቆዳና ይህን ሁሉ ግመል በለገሰህ አምላክ ስምእማፀንሃለሁ" አለው፡፡ "አያሌ ጉዳዮች አሉብኝ፥ ልረዳህአልችልም" አለው፡፡ "የማውቅህ ይመስለኛል፡፡ ሰዎችየሚፀየፉህ ለምፃምና ድሃ አልነበርክም? አሏህ ጥሩመልክና ቆዳ፥ እንዲሁም ሃብት ለገሰህ" አለው፡፡ "ከአያትቅድመ-አያቶቼ የወረስኩት ነው" አለ፡፡ "ሐሰት ከተናገርክ(አሏህ) ድሮ ወደ ነበርክበት ሁኔታ ይመልስህ" አለው፡፡ራስ-በራ ወደ ነበረው ሰው በጥንቱ መልክና አኳኋን ሆኖበመምጣትም ለዚያኛው ያለውን አለው፡፡ ይህኛውምያኛው የሰጠውን ዓይነት ምላሽ መለሰለት፡፡ "ሐሰትከተናገርክ ድሮ ወደ ነበርክበት ሁኔታህ አሏህ ይመልስህ"አለው፡፡ በጥንቱ መልክና አኳኋን እውር ከነበረው ሰውዘንድ መጣና፡- "በጉዞ ላይ እያለሁ ስንቅ የተቋረጠብኝናችግር የደረሰብኝ መንገደኛ ነኝ፡፡ ከአንተና ከአሏህከማገኛቸው ችሮታ ውጭ ለመዳረሻ የሚሆነኝ ስንቅየለኝም፡፡ ለመዳረሻዬ የሚሆነኝ አንዲት ፍየል ትሰጠኝዘንድ የዓይንህን ብርሃን በመለሰልህ አምላክ (ስም)እማፀንሀለሁ አለው ። አይነ ስውር ነበርኩ አላህ አይኔንመለሰልኝ ።ያሻህን ትተህ ያሻህን ውሰድ ።በአላህእምላለሁ ለረኡልና ሀያል ለሆነው አላህ ስል ዛሬየምትወስደውን ነገር መልስ ብዬ አላስቸግርህምአለው።ገንዘብህን ያዝ እናንተን ለመፈተን ነው የመጣሁት።አላህ በእንተ ረክቶ በሁለቱ ወላጆችህ ተቆትቶአል አለው።
(ቡኻሪ ሙስሊም)
📋ያለፈው ክፍል👇📋
https://t.me/Hafu_posts/17499
🚫ለወዳጆቻችሁ በመላክ ከአጅሩ ተካፈሉ🚫
9
8
1July 28, 2026 2.2K 11