ቃይስ ቢን አል-መሉህ ለይላ ከተባለች ሴት እብድ ያለ ፍቅር
"እኛ በምንጸልይበት ጊዜ አስሬ አትመላለስ፤ ወይ ለምን ከእኛ ጋር አትጸልይም?"
እሱም፡-"እየጸለያችሁ ነበር እንዴ?"
እነሱም፦"አዎ እየሰገድንም እየጸለይንም ነበር!"
ይሄን ሲሰማ እንዲህ አላቸው፡-
"የእውነቴን ነው በአላህ እምላለሁ አላየኋችሁም!።
የእውነቴን ነው እኔ ለይላን እንደ ወደድኳት እናንተ አላህን ብትወዱ ኖሮ
ጭራሽም ባላያችሁኝ ነበር.."


