«ናፈቅሽኝ አቦ !» ብዬ የፃፍኩት
ኩራት ሲሰማኝ - ቀድጄ ጣልኩት ።
«ናፈቅከኝ በጣም» ብለሽ የፃፍሽው
ልምምጥ መስሎሽ
ወርውረሽ ጣልሽው ።
የፍቅር ብርሃን እንዳልተሰማን
ቅር እንዳላለን እንዳልናፈቅን
በአዲስ ወረቀት - ፀብ ተላላክን ።
እንበልና ...
እኒያ ወረቀቶች ...
ቀደን የጣልናቸው
የክረምት ጎርፍ አገናኛቸው ።
እስኪ አስቢያቸው ...
ደራሽ ተሳፍረው
ሆነው ጎን ለጎን
እርስ በርሳቸው ተያይተው ቢሆን ?
ምን ይሉ ይሆን ?
By Habtamu Hadera
@getem
@getem
@paappii
93
2
2
1August 30, 2026 3.5K 44