ቃና አልባ ህይወቴ
የፈሰሰ ሀሞቴ
ጣዕም ፣
መልኩ ጠፍቶ ፡ የጠቆረ ወተቴ
ያ ‛መት ሙት አመቴ 𓏸 𓏸 𓏸
ተሰርዮልኛል ! !
....ተሰርዞልኛል...
እናትነት ፍቅርሽ ፡ ያለፍኩትን አይቶ
፤ አዝኖ ራርቶልኛል
ከአዘቅት እመቃት ፡ከባርያነት ግዞት
ለይቶ አንስቶኛል ⨳
ఎ
ማህፀንሽ ሳለሁ ኪዳን ገብተሽልኝ𓏲 አፈር ግፈሽ ቅመሽ
ያንቺን መልከ ስጋ ˔ ከእግዜር ገዝተሽልኝ
. . . አገልግለሽኛል
ተርበሽ ተጠምተሽ አሳድገሽኛል ꨄ
ርኩስ ፍጡር ወንድን በስራሽ አስንቀሽ
‟ቅድሚያ ላንተ” ብለሽ
ከሰው እኩል አርገሽ
አሁን ያለሁትን ፣
ነገ ምሆነውን . . . ሰውነቴን ሰራሽ !
{ አበጀሽ ! አበጀሽ ! }
𓏲 እናት ሴት እናቴ
ኅቡዕ ቃለ~ጥበብ ˔ የፀሎት ቅናቴ
ከፈራረስኩበት ፣
ከወለገድኩበት ፣
ደርሰሽ አንከብክበሽ ፥ በፍቅርሽ መቅናቴ ⨳
𖥔
[ ምን ትባል ፅዕዱቴ ?
. . . በምን ስም ትጠራ
ምድራዊ የሆነች የሰማያት ጣራ ]
𓏲 ስላንቺ ማንሳቱን ˔ ላልፈፅም ሰደርኩት
ላላከትም ካደምኩት
ቢሆንም
ቢሆንም እንኳንም ጀመርኩት...
< ግዴም ሆኖ ቢገኝ አበጀሁ >
by ሰምረ የሽዋስ
@getem
@getem
@getem

