ትናንትን በዛሬ_! ያቺ ትናንቴ ሀ--ሁ-- ዬ የነበረች፣ የሆነ ቀን ዛሬ ነበረች። እንድያው ሳላስብ ዘንግቻት፣… — ግጥም ብቻ 📘 — TG.ME

ትናንትን በዛሬ_!

ያቺ ትናንቴ ሀ--ሁ-- ዬ  የነበረች፣
የሆነ ቀን ዛሬ ነበረች።
             እንድያው ሳላስብ ዘንግቻት፣
             ይሄው ዛሬ አስታወስኳት።
ቁጭ ብዬ በዛሬ ፊት ስታዘባት፣
የኳተነች ጎስቋላ ፊት የነበራት፣
             በደስታ እና በፈተና የረሳዃት፣
              ይሄው አሁን በዛሬ ፊት አነሳዃት።
ከፊቴ ፊት ቁጭ ብላ ስትስቅብኝ፣
ስጠብቃት ብን ብላ እንዳጠፋኝ።
               ባትሆን ኖሮ የኔ ትናንት፣
                ይችን ዛሬ-- አሁን ባልል ታምኜባት።
መምህሬ የኔ ትናንት፣
መቆሚያዬ የዛሬ እናት፣
          የጉዞዬ እርሾ የነገዬ ርስት፣
          የጉልበቴ ሰደፍ የዘመኔ ሽበት።
                          
                     በ መ/ር ሰይድ: ነሐሴ 6, 2018

@getem
@getem
@getem
❤39👍1🔥1
August 26, 2026 6.1K 10