ውደቅ እስቲ ላንዴ እንደ ጥልያን ጦር፣ ገላህ ይሸለታል በጦር በጎራዴ። ፡ አንተ ባለ ክብር ! ላንዴ እስቲ… — ግጥም ብቻ 📘 — TG.ME

ውደቅ እስቲ ላንዴ
እንደ ጥልያን ጦር፣
ገላህ ይሸለታል
በጦር በጎራዴ።


አንተ ባለ ክብር !

ላንዴ እስቲ አቀርቅር
መታሸት ያወዛው …
ጀርባህ ይነረታል ፣
በዱላ ና በትር።
:
ተገልጠህ ብታየው
        ትከ’ሻህ ተከፍቶ
አናትህ አይተርፍም
        በኮናኝ ተሞልቶ።
.
ፅጌረዳ የሰጠህ
በዘመንህ ወራት
እሾሁን ያስቀራል
ቅጠሏን አራግፏት።
:
ከፊት ስትቀርብ አይደል?
(እንደ ለቅሶ ንፍሮ)
ተዘግነህ ‘ምታልቀው
ልኬትህ ተሽሮ ?
:
ተሞልቷል ከተማው
በድንጋይ ፣ በምሳር
ዘንበል ያልህ ጊዜ
ተቋጥሮ ያመሻል
የፈካልህ ግንባር ።
:
ብቻ!
ወንዝ እንደወረደች
የገጠር ኮረዳ ፣
ላስቲክ ጫማዋ ስር
አዳልጧት በነበር
ረጢብ  እንግጫ ፣
-
ሚዛን ስተህ ውደቅ
በቋጥኝ ፣ በጭንጫ ፤

ያጨበጨቡ እጆች
ጉያህ ይሰርጋሉ፣
ደግሞ ለቁንጥጫ ።

(ሚካኤል አ)

@getem
@getem
@paappii
❤52👍4🔥1🎉1
August 24, 2026 7.1K 16