ተኳረፍኩኝ ካገሬ ጋር
ተሳቅቄ ሆኜ ከዳር
ጀርባየን አላምነውም
ጠላቴንም አላውቀውም
ማውቀውንም አላውቀውም
ባውቀውም አልንቀውም
መተንፈሻ አጣ አገሩ
ኩፍ በዛ በየዳሩ
ሰቀቀን በርዞታል
አይጥምም አየሩ
ዘር በዛ ባገሩ
አዲስ ጠፋች በአበባ
ሚሰቴ አሏት ባለቤቴን
ቀለበቴን አይቶ አገባ
አገሯ ዳር ናት
ሰውም ወድቋል ጥጉጥጉ
ሬሳው ሳይነሳ
ዘሩን ዘሩን እየፈለጉ
አዲስ አመት ባክህ ና
አታብቅል አበባ
ኢትዬጵያን ሚሏት ሀገር
ባይሆን ይዘህ ግባ
.
.
ግዕዝ ሙላት
@geez_mulat
@getem
@getem
@getem
44
17August 23, 2026 7.2K 18