በቃኝ
-----------------------
እሳት ሆኘ ስነድ፥
አንች ቆፈን ወርሶሽ
ሎሚ ብወረውር፥
እንቧይ ሆኖ ደርሶሽ
ዝምድና ሳያንሰን፥
እየቆየሽ ባዳ መላመድ
ሳይጎድለን፥ እያደርሽ እንግዳ፤
እንግዲህ ደህና ሁኝ!
ምኞቴም በረደ፥ ቁጣየም አለፈ
ከእድሉ ጋር ታግሎ፥ ማነው-ያሸነፈ።
By Bewuketu Siyum
@getem
@getem
@paappii
79
15
6August 20, 2026 9.4K 53