ጊዜው በረረ አይድል
የሮቤል አልበምን
በቅጡ ሳንሰማ
ያን ሌት ያደርነውን
ሰፈር ሳንታማ
አመቱ ሄደ አድል
ክንፍ አበጀ አይድል
ዝም ብሎ ይበራል
አሞራ የሌለው
የዚህ ትውልድ እድል
ነይ እንሂድን ዜማ
ሌሊት ስንሳሳም
በቅጡ ሳንሰማ..
ፍፁም ሳንረጋ
ጊዜው ሄደ አይድል
ሄደን ተመለስን
ሳንመለስ ከጥል
ወድቀን ከራስ ትግል
ደግሞ ሳንዋጋ
ከፍለን የደም ዋጋ
አልጋው ፀጥ ያለበት ትግላችን
በቃ ሳንረጋ
ጊዜ በረረ አድል
ፈርቶ ዝምታችን ..
ነይ እንሂድ
ነይ አንሂድ
ሄደን ለማይቆም ጊዜ
እግራችን አይልፋ
እንኳን የሰማነው
የተሳሳምነው
ከአልጋችን እየጠፋ
አንሂድ አንሂድ
አይሰክንም አየሩ
ብዙ ነው አገሩ
ልታይ ልታይ ይላል
መስታዎት ለእውሩ
ጊዜው በረረ አድል
በእኒያ ሌሊት ከፈን
በሮቤል ዘፈን
በሀይል ተቃቅፈን
የተሻሸንበት..
የተሟሸንበት
ምናለ እንኳ
ሙዚቃ እስኪያበቃ
እግዜሩ ዘመኑን
ክንፍ ቢነሳበት
መናፈቄ እንኳ
አለመናፈቄ እንኳ
ማወላወሌ እንኳ
ሳልወስን ሳላውቀው
በረረብኝ አይድል
ትዝታ ሲነፍገኝ
የዚህ ትውልድ እድል
እንጃ ተነጫነጭኩ
ናፍቀሽኝስ አይድል??
.
.
Based on idea
ሮቤል ሚደቅሳ (ነይ እንሂድ Music )
ግዕዝ ሙላት
@geez_mulat
@getem
@getem
@getem
30
4
1August 18, 2026 9.8K 13