የተፈጥሮ ልዕልት
ልብን ካስደሰተች ቆንጆ ሴት በሳቋ
ሀሴት ትርቃለች ቀጥ ሲል ማፍቀሯ
የጨከነች ለት መሸሽ ስታበዛ
ሀዘን ይመለሳል ስትቀር ቀዝቅዛ
ፀሃይቱም ብትሆን የጠዋቷ ብስራት
የንጋቷ ኮከብ የአስራ ሁለት ሰዓት
ዓለምን ብትከብ ፀዳሏን አርብባ
ከቀን መብራት ጋር እሷም ተደርባ
እንደለመደባት ባትወጣም ጨክና
ፅልመት አትፈጥርም አይደለችም ዋና
ፋኖስም ተተኪ አምፖል ተሰባሪ
አልቃሻውም ሻማ ሲለኩሱት ቀሪ
ያቺ ጨረቃ ግን ተስፋ ግራ ሲዘም
ሞት ጥላ ሲያጠላ ስትጠበብ ዓለም
ልቦና ሲሰለብ ሰዎች ሲያንቀላፉ
መናፍስተ እርኩሳን ሲያንሰፈስፉ
ምድር ስታረምም ሸፍኗት ጨለማ
ተፈጥሮ ሲነጥቃት የድምቀቷን ግርማ
የብርሃን ልዕልት አለቃ ምስለኔ
የእስትንፋስ ያህል ጨረቃ ናት ለኔ !
ዳዊት ጥዑማይ
17/11/18
ዳ ሰኒያ ዓዲ _አሕፈሮም
@getem
@getem
@getem
31
3
2August 18, 2026 7.7K 28