አንተና እኔ የአሁን እድሜ ላይ ኗሪዎች ዛሬን አጥተን አሁን ነጥተን ለነገ አሳ አስጋሪዎች በደጉ ቀን ሳሉ… — ግጥም ብቻ 📘 — TG.ME

አንተና እኔ

የአሁን እድሜ ላይ ኗሪዎች
ዛሬን አጥተን አሁን ነጥተን ለነገ አሳ አስጋሪዎች

በደጉ ቀን ሳሉ
ለክፉ ቀን ብሎ ስንቅን መለቃቀም
ፍቅርን መጠርቀም።

ደሞ……….

ተፈቃቅረን
ተፈላልገን
ተብሰልስለን

………ደሞ ተፈራርተን

ምናባቱን ፍርሀት ከሞት መቼ ይበልጣል
አሁን ላይ ተዋዶ አሁን እንደሚ’ኖር
እራሱስ መች ያዉቃል

እዚሁ ላይ ተፋቅረን
…………. አሁን እንደሚሞት
ለነገ ሳናስቀር
……………ትእቢታችን ሰብረን
ና እንታረቅና
ነገ በኛ  ይቅና

@getem
@Tizita21
❤20🔥4😢3
August 17, 2026 8.6K 12