#አምላኬ_ሆይ
.
.
.
ለጎረምሳ ገላ፣
ከቆንጆ ሴት ሌላ።
ላንበሳ ምንጋጋ ፣
የድኩላ ስጋ ።
ለልባም እመቤት፣
የጣልያን ድርብ ድስት።
ላራሽ ለገበሬ፣
ሁለት ጥንድ በሬ ።
የምትሰጥ ፈጣሪ፣
የህዝበ አዳም መሪ።
ለጠገበ ማጣት፣
ለሰነፍ ሰው ቅጣት።
ለተዋጊ ጦሩን፣
ለሚወጣ በሩን።
ለሂያጅ ሰፊ መንገድ፣
ለሚጠይቅ ዘመድ።
ላዘነ ሰው መርሻ፣
ለተራበው ጉርሻ፣
ለጠማው ማርከሻ፣
የምትሆን መጠጊያ፣
የምትችል ትከሻ።
ላም ለገዛ በረት፣
ለበደለ ምህረት፣
ላገባ በረከት።
ለእስራኤል መና፣
ለዝናብ ደመና።
ለጌቶ ብርንዶ፣
ለእንቦሳ ሰርዶ።
ለጴጥሮስ መረብ፣
ለላሜህ ልጅ መርከብ።
ለዳዊት መንግስቱን፣
ለእዮብ ትዕግስቱን።
የቸርካቸው አባት፣
የሌለህ ደም ግባት።
ጎዶሎን የምትሞላ፣
ጥብቁን የምታላላ።
እደጅህ ላይ ካረፈው፣
ሞልቶ ከተረፈው።
ለኔም ሰው አታጣም፣
ይልቅ ስጠኝና፤
ላመስግንህ በጣም !!🙏🙏🙏
✍️ ዓቢይ ( @abiye12 )
@getem
@getem
@getem
81
36
8
4August 17, 2026 8.4K 77