እኔ ያንቺን ውበት በቋሚነት ማደንቅ፣ ብዙ ሰው አየሁኝ እውነትን ሲደብቅ፡፡ እኔስ አያስችለኝ፧ መኳል ነው… — ግጥም ብቻ 📘 — TG.ME

፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
እኔ ያንቺን ውበት በቋሚነት ማደንቅ፣
ብዙ ሰው አየሁኝ እውነትን ሲደብቅ፡፡
እኔስ አያስችለኝ፧
መኳል ነው ማስሸብረቅ ባለቀው ማማርሽ፣
አይቶ ዝም ሲል ግን ስንቱን ታዘብኩልሽ?!
ይቺ ጠባብ ቤቱ ትዕቢቱ ከልክላው
እንጂ የማይስልሽ፧
ዝምታ ሲያበዛ መልስ ያጣ እንዳይመስልሽ፨
//ክብሬን ክሬን ሲል ነው የማያወድስሽ//
(ወትሮም በዚ አገር
          አብሰልሳይ ይቀድማል፧
                                    ከሚያቆላጵስሽ!)

@mypoems396
@getem
@getem
@getem
❤34🔥7🎉3
August 12, 2026 10.3K 21