" ሩቅ ናፋቂ መሆን የለብንም" አርበኛ አንተነህ ድረስ የጎንደር ፋኖ ፖለቲካ ዘርፍ ሀላፊ
Anteneh Dires
የራስን ችግሮች በራስ አቅም መፍታትና በጠንካራ መሠረት ላይ መቆም ለዘላቂ ውሳኔ እና ነፃነት ዋናው መሠረት ነው።
ትናንት በወንድሞችህ ላይ እንድትዘምትና ደም እንድትቃባ ስምሪትና ግዳጅ የሰጠ አካል፣ ነገ ደግሞ በሌላ ምክንያት በገዛ ራስህ ላይ ላለማዝመቱና እሚፈልገውን ዓላማ ላለማስፈፀሙ ምንም ዓይነት ዋስትና የለም።
በመሆኑም ከውጭ ከሚመጣ ጊዜያዊ ትብብር እና የወደፊቱን ዕድል በማያስተማምን አካል ላይ መጣልና የሩቅ ናፋቂ መሆን ተገቢ አይደለም፤ የሩቅ እገዛ ከውጭ ሲያዩት የቀረበና አጋር የሚመስል ቢሆንም፣ ውስጡ ግን በራስ ጥቅም ላይ የተመሠረት ያደረገ ታማኝነት የሌለው ሊሆን ይችላል።
በእውነትና በተግባር አብሮህ የሚቆመውና ሊደርስልህ የሚችለው ከጎንህ ያለው ወንድምህ ብቻ ነው። የደም፣ የባህልና የጋራ ታሪክ ቁስልም ሆነ ደስታ በጋራ የሚጋራው ቅርብህ ያለው ወንድም ስለሆነ፣ ልዩነቶችን በውይይትና በውስጥ አቅም መፍታት ይበልጥ አስፈላጊ ይሆናል።
የውጭ ተፅዕኖዎችና ጊዜያዊ ወዳጅነቶች ሲቀያየሩ፣ የደምና የቅርብ ወንድምነት ትስስር ግን ዘላቂ ነው። በመሆኑም መፍትሔውን ከውጭ ከሚመጣ የሩቅ ናፍቆት ይልቅ በመካከላችሁ ባለው እውነተኛ ወንድማማችነትና የጋራ ውይይት ውስጥ መፈለግ የመጨረሻውና አስተማማኙ መንገድ ነው።
አሸናፊነታችን አድነታችን ላይ ነው!
August 30, 2026 99