MIC Fourth Batch Student: post #820 — TG.ME

❇️ሜሪላንድ ኢንተርናሽናል ኮሌጅ የሜሪ ጆይ ኢትዮጲያ የ "Silver Level Membeship" የክብር አጋር ሆነ!!!

ላለፉት 30 አመታት በበጎ አድራጎት ስራ ግምባር ቀደም ከሆኑት የሚጠቀሰው ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ: ሜሪላንድ ኢንተርናሽናል ኮሌጅ የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ የ " Silver Level Membership" የክብር አባል በመሆን  ከሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ መስራች ከሆኑት ሲ/ር ዘቢደር ዘውዴ የእውቅና ሰርተፍኬት በሜሪላንድ ኢንተርናሽናል ኮሌጅ ፕሬዝደንት ዶ/ር ዮናስ (ረ/ፕሮፌሰር)  በኩል ተበረከተለት!!!

በተለያዮ በጎ አድራጎት ስራዎች በንቃት የሚሳተፈው ሜሪላንድ ኢንተርናሽናል ኮሌጅ ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ ለሚያከናውነውን የበጎ አድራጎት ስራ የ " Silver Level Membership" የክብር አባል በመሆኑ መላው የተቋሙን ፕሮፌሰሮች : ሰራተኞች: የቀድሞ ተመራቂዎች እና ተማሪዎች እንኳን ደስ አላችሁ እያልን ኮሌጃችን ከዚህ በፊትም ከትምህርት ክፍያ ላይ ከነፃ እስከ ግማሽ የትምህርት እድል:-

ለየኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (INSA) ኃላፊዎች እና ሠራተኞች

ለኢምግሬሽን ኃላፊዎች እና ሰራተኞች

ለሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሰራተኞች

ለገቢዎች ሚኒስቴር ኃላፊዎች እና ሰራተኞች

ለተለያዮ የመንግስት ተቋማት ሰራተኞች በመስጠት እንዲሁም:-

👉 ለእናት የበጎ አድራጎት ድርጅት

👉 ለኢትዮጲያ ኢንፎርሜሽን ሲስትምስ ማህበር የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ የማህበረሰብ አገልግሎት ላይ የበኩሉን ድርሻ እያበረከተ መሆኑን ይታወቃል::

Community Service Unit
Maryland International College
👍2
August 10, 2026 115 1