ፍልስፍና እና የፍልስፍና አባባሎች: post #448 — TG.ME

አለማችን ላይ ያሉ ሀገሮች ሁለት አይነት ሀብት አላቸው! የጭንቅላትና የመሬት አፍሪካውያን የመሬቱ ተባርኮላቸዉ ጭንቅላት ላይ ግን ችግር አለ። እነ ጃፓን ደግሞ መሬቱ በየአመቱ በሱናሚ የሚናወጥ ሀገር ነው። ነገር ግን ሱናሚ የጃፓንን ህንፃዎች እንጂ የጃፓንን ጭንቅላት ማፍረስ አይችልም። ጃፓን ለኮንጎ ዛዬር እርዳታ ትልካለች የሁለቱን ሀገር የተፈጥሮ ሀብት ልዩነት ካዬነዉ ልዩነቱ የተአምር ያህል ነው። ዛዬር ነበረች እርዳታ መላክ የነበረባት ግን መሬቱ ተባርኮ ጭንቅላት ስለጠፋ አስር ኩንታል ጤፍ እቤት ዉስጥ ቢኖር አስፈጭቶ ካልተበላ ከርሃብ ማምለጥ አይቻልም። ስለዚህ አስተሳሰብ ላይ ትልቅ ስራ መስራት ይገባናል። ለዚህም ደግሞ ትልቁ መንገድ ማንበብ ነው። ያላነበበ ጭንቅላት ጥሩ ሀሳብና ጠቃሚ ነገር ማመንጨት አይችልም! የዘወትር ስራው አሲድ ማመንጨት ነው ስለዚህ እናንብብ! እናንብብ! እናንብብ! #መጋቢ _ሀዲስ_እሸቱ

October 7, 2021 24.8K 54