የፌዴራል ሥነምግባር እና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ዜጎችን በፀረ-ሙስና ትግል ይበልጥ ለማሳተፍ እና የሙስና… — Federal Ethics And Anti- Corruption Commission — TG.ME

የፌዴራል ሥነምግባር እና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ዜጎችን በፀረ-ሙስና ትግል ይበልጥ ለማሳተፍ እና የሙስና ወንጀሎችን ለሕዝብ በግልጽ የማጋለጥ እንዲሁም አግባብነት ያላቸው የተጠያቂነት ሥራዎች በቁርጠኝነት እንዲፈጸሙ ዘርፈ-ብዙ እና የተቀናጁ የፀረ-ሙስና ትግል ሥራዎች በ2019 በጀት ዓመት ሥራ ላይ እንዲውሉ ርብርብ ይደረጋል።

በተለይም፣ የተለያዩ የመደበኛ እና ማህበራዊ ሚዲያ አውታሮችን በመጠቀም የሙስና ወንጀሎችን በተጨባጭ ማስረጃ ላይ ተመስርቶ የማጋለጥ እርምጃዎችን ያካትታል። በመሆኑም፣ ዜጎች የሙስና ወንጀል ሥጋትና ተጋላጭነት ያለባቸው የተቋማት አሰራር ሥርዓት (የመንግሥት፣ የልማት ድርጅቶች፣ ሕዝባዊ ድርጅቶች፣ የግል ድርጅቶች) ሲያጋጥማችሁ ለኮሚሽኑ ከተጨባጭ ማስረጃ ጋር በመጠቆም ለሰላ የፀረ-ሙስና ትግል በትብብር እንፈጽም።

ሙስና የጋራ ጠላታችን ነው፣ በህብረት እንታገል!

የሙስና ወንጀል መጠቆሚያ አማራጮችን፣ ወቅታዊ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት👇🏾

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች

https://play.google.com/store/apps/details?id=com.codewaveet.ecis

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች

https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id659366231

ለሀብት ማሳወቅና ምዝገባ፦ https://feaccears.gov.et/

ዌብሳይት፦ https://www.feacc.gov.et

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/

ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc

ዩትዩብ፡- https://www.youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149

ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
August 31, 2026 418 4