የክረምት በጎ ፍቃድ ሥራ አካል የሆነው የወጣቶች የሥነምግባር ማነቃቂያ ሥልጠና በቂርቆስ ክፍለ-ከተማ ተካሄደ
***
(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ነሐሴ 23/2018 ዓ.ም አዲስ አበባ) የፌደራል የሥነምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን የክረምት በጎ ፍቃድ ሥራ አካል የሆነው የወጣቶች የሥነምግባር ማነቃቂያ ሥልጠና በቂርቆስ ክፍለ-ከተማ አካሂዷል።
በመድረኩ የተገኙት ኮሚሽኑ የሙስና መከላከል ጥናት ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር አቶ እሸቴ አስፋው፣ ኮሚሽኑ በትውልድ ሥነምግባር ግንባታ፣ በሙስና ቅድመ መከላከልና ሕግ ማስከበር ላይ ትኩረት አድርጎ እየሠራ መሆኑን ገልጸዋል።
የሙስና መከላከል ሥራውን ውጤታማ ለማድረግ የኮሚሽኑ አሠራሮች ዲጂታላይዝ እየተደረጉ መሆናቸውን ጠቁመው፣ ዲጂታል የሀብት ምዝገባ ሥርዓት(Ethiopian Asset Registration - EARS) እና ብሔራዊ የሙስና ወንጀል መረጃ ጥቆማ የዲጂታል አሠራር ሥርዓት (National Corruption Reporting System -NCRS) ከተዘረጉት የዲጂታል አሠራሮች መካከል ተጠቃሽ መሆናቸውን አስረድተዋል።
ወጣቶች በሥነምግባር አርአያ በመሆን ሙስናንና ብልሹ አሠራርን በትጋት መታገል አለባቸው፣ ይህም ለበለጸገችና የተሻለች ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ ወጣቶች የሚጫወቱት ሚና የጎላ መሆኑን አመላክተዋል።
የወጣቶች የሥነምግባር ማነቃቂያ ሥልጠናውን የኮሚሽኑ የሥነምግባርና ፀረ-ሙስና ሥልጠና መሪ ሥራ አስፈፃሚ አቶ የኃላሸት ደሳለኝ ሰጥተዋል።
በሥልጠናው መጨረሻ ሰልጣኞች በቀረቡት ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ ጥያቄዎችንና አስተያየቶችን ያቀረቡ ሲሆን፣ በጥያቄዎቹና በተነሱ ሀሳቦች ላይም ማብራሪያና ምላሽ ተሰጥቷል።
ትውልድን በሥነምግባር፣ ተቋምን በአሰራር!
የሙስና ወንጀል መጠቆሚያ አማራጮችን፣ ወቅታዊ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት👇🏾
#NCRS ሞባይል መተግበሪያ
#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.codewaveet.ecis
#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id659366231
ለሀብት ማሳወቅና ምዝገባ፦ https://feaccears.gov.et/
ዌብሳይት፦ https://www.feacc.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
ዩትዩብ፡- https://www.youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
Google Play
NCRS - Apps on Google Play
Report corruption in Ethiopia securely. Track progress & fight injustice.
August 29, 2026 1.1K 1