ሀሰተኛ ሰነዶችን ሲያዘጋጅ የነበረ ግለሰብ ላይ ክስ ተመሰረተ
***********************
(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ነሐሴ 21/2018 ዓ.ም አዲስ አበባ) በአዲስ አበባ ከተማ ጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8፣ አዲሱ ገበያ አካባቢ በሚገኝ የገበያ ማዕከል ውስጥ ሀሰተኛ ሰነዶችን ሲያዘጋጅ ነበር የተባለ ግለሰብ ላይ ክስ መመስረቱን ፖሊስ ገለጸ።
የጉለሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ ኢንተለጀንስ በተከታታይ ሦስት ቀናት ባደረገው ክትትልና ቁጥጥር፣ ካሊድ አወል የተባለ ግለሰብ ሀሰተኛ ሰነዶችን ሲያዘጋጅ እንደነበር ተጠርጥሮ በሚሰራበት የህትመት ድርጅት ላይ ብርበራ መካሄዱን ገልጿል።
በተካሄደው ብርበራም በተለያዩ የመንግሥት ተቋማት ስም የተዘጋጁ ሀሰተኛ ሰነዶችና ለማምረት የሚያገለግሉ የህትመት መሣሪያዎች መገኘታቸው ተመላክቷል።
ከተያዙት ማስረጃዎች መካከል የጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 እና የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 ወሳኝ ኩነት ሰነዶች፣ የየካ ክፍለ ከተማ ሰነዶች ማረጋገጫ ጽሕፈት ቤት ራስጌና ክብ ማህተም፣ የልደት ምስክር ወረቀት፣ የአዲስ አበባ ከተማ ገቢዎች ቢሮ የግብር አከፋፈል ማስረጃ፣ የፌዴራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ቢሮ የፎረንሲክ ማስረጃ እና ዓመታዊ የተሽከርካሪ ምርመራ ማስረጃ ይገኙበታል።
በተጨማሪም ሀሰተኛ ሰነዶችን ለማዘጋጀት ይጠቀምባቸው ነበር የተባሉ ሁለት ዴስክቶፕ ኮምፒውተሮች፣ ፍላሾችና ፕሪንተር መያዛቸውን ፖሊስ አስታውቋል።
ፖሊስ በማስረጃ ያጠናቀረውን የምርመራ መዝገብ ለክፍለ ከተማው ዐቃቤ ሕግ በመላክ፣ በግለሰቡ ላይ ክስ እንዲመሰረት መደረጉን የአዲስ አበባ ፖሊስ በፌስቡክ ገጹ አስታውቋል።
ትውልድን በሥነምግባር፣ ተቋምን በአሰራር!
የሙስና ወንጀል መጠቆሚያ አማራጮችን፣ ወቅታዊ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት👇🏾
#NCRS ሞባይል መተግበሪያ
#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.codewaveet.ecis
#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id659366231
ለሀብት ማሳወቅና ምዝገባ፦ https://feaccears.gov.et/
ዌብሳይት፦ https://www.feacc.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
ዩትዩብ፡- https://www.youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
Google Play
NCRS - Apps on Google Play
Report corruption in Ethiopia securely. Track progress & fight injustice.
August 27, 2026 1.7K 8