እንኳን ለነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) የልደት በዓል (መውሊድ) በሰላም አደረሳችሁ! * የፌዴራል የሥነምግባርና… — Federal Ethics And Anti- Corruption Commission — TG.ME

እንኳን ለነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) የልደት በዓል (መውሊድ) በሰላም አደረሳችሁ!

*

የፌዴራል የሥነምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ሳሙኤል ኡርቃቶ (ፒ.ኤች.ዲ) ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች 1 ሺህ 501ኛውን የነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) የልደት በዓል (መውሊድ) አስመልክቶ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ኮሚሽነሩ በመልዕክታቸው፣ የነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ሕይወትና ትምህርቶች በሰላም፣ በፍትሕ፣ በታማኝነትና በመልካም ሥነምግባር መኖርን የሚያስተምሩ ናቸው። እነዚህ እሴቶችም ሙስናን በመከላከልና ሀብትን በአግባቡ በመጠበቅ ረገድ የሁላችንም የጋራ ኃላፊነት መሠረት ነው።

መውሊድን ስናከብር፣ በእምነታችን የምናከብራቸውን የታማኝነት፣ የፍትሕና የሥነምግባር እሴቶች በዕለት ተዕለት ሕይወታችንና በሥራ ቦታችን በተግባር ለማሳየት ቃል በመግባት መሆን ይኖርበታል። ሙስናን መታገል የመንግሥት ብቻ ኃላፊነት ሳይሆን፣ የእያንዳንዱ ዜጋ የጋራ ኃላፊነት ነው።

በተለይም ሐቀኝነትን በመምረጥ፣ የሕዝብን ሀብት በመጠበቅ፣ ሙስናን በመታገልና በመልካም ሥነምግባር በመመራት፣ ንጹሕ፣ ፍትሐዊና ተጠያቂ ማኅበረሰብ ለመገንባት የየራሳችንን አስተዋጽኦ እናድርግ።

መልካም በዓል!
August 25, 2026 1.6K 1