በትምህርት ዘርፍ የሥነምግባርና ፀረ-ሙስና ሥራ አስፈፃሚዎች የ2018 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀምና በ2019… — Federal Ethics And Anti- Corruption Commission — TG.ME

በትምህርት ዘርፍ የሥነምግባርና ፀረ-ሙስና ሥራ አስፈፃሚዎች የ2018 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀምና በ2019 በጀት ዓመት እቅድ ላይ ግምገማዊ ውይይት ተካሄደ

**

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ነሃሴ 18/2018 ዓ.ም አዲስ አበባ) የፌዴራል የሥነምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን የትምህርት ዘርፍ የሥነምግባርና ፀረ-ሙስና ሥራ አስፈፃሚዎች የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርትና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ ግምገማዊ ውይይት አካሂዷል።

የግምገማዊ ውይይቱ ዓላማ በ2018 በጀት ዓመት በመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተከናወኑ የፀረ-ሙስና ትግል እንቅስቃሴዎችን፣ የዳሰሳ ጥናት ውጤቶችን፣ የድጋፋዊ ሱፐርቪዥን ረቂቅ ሪፖርትን እና የዕቅድ አፈፃፀሙን መገምገም፣ እንዲሁም የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ በመወያየት የቀጣይ አቅጣጫ ለማስቀመጥ ነው።

በመድረኩ የኮሚሽኑ የሙስና መከላከል ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር ክቡር አቶ እሸቴ አስፋው እንደገለጹት፣ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚገኙ የሥነምግባር አምባሳደር ተማሪዎች የሥነምግባር ግንባታና የሙስና መከላከል ሥራዎችን እንዲያግዙ በተገቢው መልኩ ተሳትፏቸውን ማጠናከር ይገባል።

በተለይም የዩኒቨርሲቲ አመራሮች የፀረ-ሙስና ትግሉን በባለቤትነት የመምራት ኃላፊነታቸውን በተገቢው ሊወጡ እንደሚገባ አፅንዖት ሰጥተዋል።

በቀጣይም በሦስቱ የፀረ-ሙስና ትግል ምሰሶዎች ማለትም በሥነምግባር ግንባታ፣ ቅድመ ሙስና መከላከልና ሕግ ማስከበር ሥራዎች ላይ በትኩረት እንደሚሠራ ጠቁመው፥ የሥራውን ውጤታማነት ለማሳደግ የተጀመረውን የድጋፍና ክትትል ሥራ እንዲሁም ቅንጅታዊ አሠራርን ማስቀጠል እንደሚገባ ገልጸዋል።


የኮሚሽኑ የሥነምግባር ግንባታ ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር ክቡር አቶ ፍቃዱ ሰቦቃ በበኩላቸው፣ ተቋማት የሚሰጧቸውን አገልግሎቶች ሥነምግባራዊ በማድረግ ብልሹ አሠራሮችን ማስወገድ ይገባል ብለዋል።

የሚሰጡ የሥነምግባር ግንባታ ሥልጠናዎችም በተቋማት የሚገኙ ክፍተቶችን በመለየት ችግር ፈቺ እንዲሆኑ ማድረግ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

በቀጣይም ለሥነምግባር አምባሳደር ተማሪዎች ተገቢውን ሥልጠና በመስጠት፣ ብልሹ አሠራሮችን በመከላከል ላይ በትኩረት እንዲሠሩና ለፀረ-ሙስና ትግሉ አጋዥ እንዲሆኑ ማድረግ እንደሚገባ አሳስበዋል።

በግምገማዊ ውይይቱ የተሳተፉት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትና የፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች የሥነምግባርና ፀረ-ሙስና ሥራ አስፈፃሚዎችም ሀሳብ፣ ጥያቄና አስተያየቶችን አቅርበዋል። በተነሱት ጉዳዮችም ላይ ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቷል።

ትውልድን በሥነምግባር፣ ተቋምን በአሰራር!

የሙስና ወንጀል መጠቆሚያ አማራጮችን፣ ወቅታዊ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት👇🏾

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች

https://play.google.com/store/apps/details?id=com.codewaveet.ecis

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች

https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id659366231

ለሀብት ማሳወቅና ምዝገባ፦ https://feaccears.gov.et/

ዌብሳይት፦ https://www.feacc.gov.et

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/

ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc

ዩትዩብ፡- https://www.youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149

ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
Google Play
NCRS - Apps on Google Play
Report corruption in Ethiopia securely. Track progress & fight injustice.
August 25, 2026 1.3K 2