የአየር ወለድ ሻምበሎች በፅንፈኛ ቡድን ላይ እርምጃ ወሰዱ።
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ጳጉሜ 01 ቀን 2018 ዓ.ም
በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን መርሀ-ቤቴ ወረዳ እና ሚዳ ወረሞ ወረዳ የሚንቀሳቀሰው የፅንፈኛ ቡድን በአየር ወለድ ሻምበሎች መደምሰሱን የአየር ወለድ ክፍለ ጦር አዛዥ ኮሎኔል ማትዮስ ማዴቦ አስታወቁ።
በሰሜን ሸዋ ዞን መርሐ-ቤቴ ገረን ቀበሌ እና በሚዳ ወረሞ ወረዳ አላባ ቢራቦ ቀበሌዎች በመንቀሳቀስ ህዝቡን በመዝረፍ፣ በማስጨነቅና ቀረጥ በመሰብሰብ ላይ የነበረውን የጥፋት ቡድን የአየር ወለድ ሻምበሎቹ ክትትል በማድረግ እርምጃ መውሰዳቸውን አዛዡ ገልፀዋል።
ኮሎኔል ማትዮስ በጥፋት ቡድኑ አጠራር ናደው ክፍለጦር ዘመቻ ሃላፊ መኳንንት ሽመልስን ጨምሮ ከ15 በላይ በየደረጃው የሚገኙ አመራርና አባላት የተደመሰሱ መሆኑንና የጥፋት ቡድን አባላት መማረካቸውንና መቁሰላቸውን እንዲሁም የነፍስ ወከፍ መሳሪያና የመገናኛ ሬዲዮ መማረኩን አብራርተዋል ። ዘገባው የአየር ወለድ ክፍለጦር የሠራዊት ስነ-ልቦና ግንባታ ነው
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
https://dfmc.mod.gov.et/
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0
https://www.facebook.com/fdredefense.official
16
9
7
3September 6, 2026 3K 3