የአሽከርካሪዎችን ብቃት በማረጋገጥ የትራፊክ አደጋን ማሰወገድ እንደሚገባ ተገለፀ።
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ጷጉሜ 01ቀን 2018 ዓ.ም
የአሽከርካሪዎችን ብቃት በማረጋገጥና የተሽከርካሪ ደህንነት በመጠበቅ የትራፊክ አደጋን ማሰወገድ እንደሚገባ የሰሜን ምዕራብ ዕዝ ትራንስፖርት ኃላፊ ኮሎኔል ታደለ ገረመው ተናገሩ።
የሰሜን ምዕራብ ዕዝ ትራንስፖርት በትራፊክ አደጋ መንስኤዎችና በመፍትሄዎቻቸው ዙሪያ ላይ ያተኮረ የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት ለዕዙ አመራሮች ሰጥቷል።
አመራሩ የአሽከርካሪዎችንም ሆነ የተሽከርካሪዎችን ደህንነት የመከታተል፣የመቆጣጠርና ሊከሰቱ የሚችሉ አደጋዎችን የመቆጣጠር ኃላፊነት አለበት ያሉት ኮሎኔል ታደለ ገረመው በቸለልተኝነት ጥፋት በሚፈፅሙት አሽከርካሪዎችም ተገቢውን የእርምት እርምጃ በመውሰድ ማስተማር ይገባልም ብለዋል።
አሸከርካሪዎች ውድ የሆነውን የሰው ህይወትና ከፍተኛ ሃብት የወጣበት የተቋሙን ንብረት የሚያጓጉዙ በመሆናቸው የጥንቃቄ ደንቦችን ማሟላታቸውን ማረጋገጥ የሁሉም አመራር ኃላፊነት ስለመሆኑም ተናግረዋል።
የዕዙ ትራንስፖርት ብቁ አሽከርካሪዎችን ለማፍራት ከመከላከያ ትራንስፖርትና ከአዋሽ የውጊያ ቴክኒክ ትምህርት ቤት የወታደራዊ ተሽከርካሪ አሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ ጋር በመተባበር ስልጠና በመስጠት አደጋዎችን ለመቀነስ ውጤታማ ተግባራት እየተከናወኑ ነው ብለዋል።
ዘጋቢ አለምፀሃይ ተሾመ
ፎቶግራፍ አበራሽ ተሰፋዬ
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
https://dfmc.mod.gov.et/
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0
https://www.facebook.com/fdredefense.official
16
10
1September 6, 2026 2.6K