በ7ኛ ሜካናይዝድ ክፍለ ጦር ሲካሄድ የቆየው ስፖርታዊ ውድድር ተጠናቀቀ።
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ጷጉሜ 01 ቀን 2018 ዓ.ም
በ7ተኛ ሜካናይዝድ ክፍለ ጦር ሻለቆች እና ስታፍ መምሪያዎች መካከል ሲካሄድ የቆየው የስፖርት ውድድር የክፍለ ጦሩ አመራሮችና ሲቪል አመራሮች በተገኙበት ፍፃሜውን አግኝቷል።
ውድድሩ በእግር ኳስ፣ በመረብ ኳስ፣ በተኩስ፣ በቴንስና በገመድ ጉተታ የተካሄደ ሲሆን አሸናፊ ቡድኖች ኮከብ ተጫዋች፣ ኮከብ ግብ አግቢ እና የ5ኪሎ ሜትር ሩጫ አሸናፊዎች የምስክር ወረቀት ተሰጥቷቸዋል።
የ7ኛ ሜካናይዝድ ክፍለ ጦር አዛዥ ኮሎኔል ፎቶ ይሰማው በስፖርት የዳበረ ሠራዊት የድል ባለቤት መሆኑ የማይቀር መሆኑን ገልፀው ስፖርት በፍቅር በወዳጅነት እና በመተሳሰብ ከተካሄደ ይበልጥ የጋራ አንድነትን እንደሚፈጥር አሥረድተዋል። ዘገባው የክፍለ ጦሩ የሠራዊት ስነ ልቦና ግንባታ ነው።
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
https://dfmc.mod.gov.et/
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0
https://www.facebook.com/fdredefense.official
34
4
1September 6, 2026 3.9K