የበዓል ወቅት የሳይበር ጥንቃቄ የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ጷጉሜ 02 ቀን 2018 ዓ.ም በበዓላት ወቅት… — FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት — TG.ME

የበዓል ወቅት የሳይበር ጥንቃቄ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ጷጉሜ 02 ቀን 2018 ዓ.ም

በበዓላት ወቅት የገንዘብ ዝውውር እና የሸመታ ፍላጎት ስለሚጨምር፣ የሳይበር ወንጀለኞች ይህንን አጋጣሚ ለጥቃት ይጠቀሙበታል። ሰዎች በደስታ እና በችኮላ ላይ ስለሚሆኑ፣ የሚላኩላቸውን የማታለያ መልእክቶች በጥልቀት ሳይመረምሩ የመቀበል እድላቸው ከፍተኛ ነው። አጭበርባሪዎች "ትልቅ ሽልማት አሸንፈዋል" በሚሉ መልእክቶች የግል እና የባንክ መረጃዎችን ለማግኘት ይሞክራሉ።

እንዲሁም፣ የሐሰት ማስፈንጠሪያዎችን (Phishing Links) በመላክ የይለፍ ቃላትን እና የባንክ አካውንት መረጃዎችን ይሰርቃሉ። "ቅናሹ ሊያበቃ ነው፣ ይፍጠኑ..." በሚል የችኮላ ስሜት በመፍጠርም ገንዘብ እንዲላክላቸው ያደርጋሉ።

ራሳችንን ለመጠበቅ፣ ያልተረጋገጡ የሽልማት እና የቅናሽ መልእክቶችን እንዲሁም አጠራጣሪ ሊንኮችን ፈጽሞ አለመጫን ያስፈልጋል። የክፍያ ጥያቄዎችን ትክክለኛነት በስልክ ወይም በይፋዊ መተግበሪያዎች ማረጋገጥ እና የባንክ መለያዎችን በሁለት ደረጃ ማረጋገጫ (Two-Factor Authentication) ማጠናከር አስፈላጊ ነው። የግል ሚስጥራዊ ቃላትን (PIN/Password) ለማንም አሳልፎ አለመስጠትም አስተማማኝ ጥንቃቄ ነው።
የመከላከያ የሳይበር ማዕከል

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
https://dfmc.mod.gov.et/

https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

https://www.facebook.com/fdredefense.official
❤26👏10👍2🔥1
September 7, 2026 4.5K 2