የምሥራቅ ዕዝ ስታፍ የሠራዊት አባላት ደም ለገሱ፡፡
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት መስከረም 08 ቀን 2019 ዓ.ም
የምስራቅ ዕዝ ስታፍ የሠራዊት አባላት ለሐረሪ ክልል ጤና ቢሮ ደም ባንክ አገልግሎት ደም ለገሱ፡፡
ሀገራዊ ተልዕኮውን በብቃት እየተወጣ ያለው የምስራቅ ዕዝ ድጋፍ ሰጭ ሃይሉ ከተልዕኮው ባሻገር በልዩ ልዩ ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ እየተሳተፈ ህዝባዊነቱን በተግባር ያረጋገጠ ነው።
አባላቱ በደም እጥረት ምክኒያት ሊከሰት የሚችልን ሞት እና ተያያዥ ችግሮችን ለመቅረፍ የራሳችንን አስተዋፅኦ ማበርከት ይገባል በሚል እሳቤ ለሐረሪ ክልል ጤና ቢሮ ደም ባንክ ደም ለግሰዋል፡፡
አስተባባሪው የምስራቅ ዕዝ ሴቶች ጉዳይ ሃላፊ ሌተናል ኮሎኔል ጁሃራ ከማል የምስራቅ ዕዝ ስታፍ አባላት ደም ሲለግሱ የመጀመሪያቸው እንዳልሆነ ገልፀው በደም እጥረት ምክኒያት ሊከሰት የሚችልን ሞት እና ተያያዥ ችግሮችን ለመቅረፍ የሚቻለው በፍቃደኝነት ደም ሲለግስ በመሆኑ ሰራዊታችን ይህን በመረዳት በተደጋጋሚ ጊዜ ደም እየለገሰ ይገኛል ብለዋል፡፡ ዘገባው የምስራቅ ዕዝ ሚዲያ እና ህዝብ ግንኙነት ነው፡፡
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
https://dfmc.mod.gov.et/
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0
https://www.facebook.com/fdredefense.official
28
5
3
3
1September 18, 2026 3.2K